Monday, December 31, 2012

የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ያገባኛል

የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ያገባኛል

ሁላችንም የእምነቱ ተከታዮች ማለትም የቤተ ክርስቲያን ችግርና ጉዳይ የሚያሳስበንና የሚያስጨንቀን ሁሉ ይህን አዋጅ አውጀን በሃዘንና በሃሳብ ውስጥ ከሰመጥን ብዙ ቀናትን በማሳለፍ ላይ እንገኛለን። በእርግጥ ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ደም የተመሰረተች ስለሆነች ፈተናዋም ልክ እንደ ኢየሱስ ክርስቶ ይበዛባታል ይጸናባታል። መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይችን ቤተክርስቲያን በደሙ ለመመስረትና የአዳምን ዘር በሙሉ ድህነት ለማዎጅ ወደዚህ ዓለም ከመጣ  ከውልደቱ ጀምሮ እስከ ትንሳኤው ድረስ በፈተና በመከራ ውስጥ እንደነበረ ሁላችንም እለት እለት የምናስታውሰው የእምነታችን መሰረት ነው። ስለዚህ ፈተና ለቤተ ክርስቲያን አዲስ እንግዳ ነገርም አይደለም፤ በተለያየ ጊዜ አይነቱንና መጠኑን እየቀያየረ አንገላቷታል፣ አሰቃይቷታል ልጆቿም አንገታቸውን ለሰይፋና ለስለት፣ ጀርባቸውን ለግርፋት ሰጥተው ሰማትዕነት ተቀብለውላታል። ዛሬም እኛ ይህንን አዋጅ ስናውጅ የክርስቶስን ጽዋትዎ መከራ፣ አባቶቻችን የተቀበሉትን ሰማዕትነት በማሰብ እንጂ ዝም ብለን ዛሬ ላይ ዘመኑ ያፈራቸውን ብሔርተኝነት፣ ወገንተኝነትና ፓለቲካ ተከትለን እንዳልሆነ የሚመለከተው ሁሉ እንዲያውቅልን በአጽንኦት መግለጽ እወዳለው። 
ቤተ ክርስቲያን በዋናነት በዘመነ ሰማዕታት፣ በዘመነ ዮዲት፣ በዘመነ ግራኝ ሙሀመድ፣ በዘመነ ሱስንዮስ፤ የትናቱን እንኳ የቅርቡን የፋሽስት ኢጣሊያ እንዲሁም በተለያየ ጊዜ ከውስጥም ከውጭም የደረሰባትን  ከባድ ፈተናዎች እንደ አመጣጣቸው አሳልፋለች ዛሬም በፈተና ውስጥ መኖሯ ለትክክለኛ አማኝ ብዙም ከባድ አይሆንም። ሆኖም ግን ዛሬ ላይ የገጠማት ፈተና እንዲህ በቀላሉ ልናልፈው የምንችለው ጉዳይ አይደለም። ምክንያቱም አባቶቻችን ከላይ ያነሳናቸውን ፈተናዎች ድል የነሱት በእግዚአብሔር ረዳትነት እና በአንድነት፣ በህብረትና በመወያየት እንጂ በመለያየት አልነበረም "ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" የሚለውን ብሂል በመጠቀም እንጂ። አንድ ነገር ግን ማሰብ ያለብን አገርንም፣ ቤተክርስቲያንንም ማንኛውንም ነገር መለያየትና መከፋፈል የሚጎዳንን ያክል ሌላ ምንም ነገር አይጎዳንም። ታላቁ አባታችን ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ በትምህርታቸው "የቤተ ክርስቲያን ሕይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛባታል፤ ስለዚህ የቤተክርስቲያንን አቋም፡ አንድነት አጠናክሩ" በማለት ነበር ለቤተ ክርስቲያን ጠበቃ እንድንሆን ያስተማሩን። ለዛም ነው እኛ  ሁላችንም "የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ያገባኛል" የሚል አዋጅ አውጀን በቻልነው መጠን ለቤተ ክርስቲያን ማነኛውም ችግር መፍትሔ ለማፈላለግ ወደኋላ የማንል መሆኑን እየገለጽን ያለነው። ነገር ግን  የቃሉን አዋጅ እንዴት ወደተግባር ለውጠን ቤተ ክርስቲያንን ከመለያየት ወደ አንድነት፣ ወደ ፍቅር፣ ወደ ሰላምና መረጋጋት እናምጣ የሚለው የሁላችንም መልስ ያላገኘንለት ጥያቄ ነው። ለዚህ ጥያቄ በቀላሉ መልስ ለአለማግኘትና ለችግሩም መንስሄ የሆኑትን በጥቂቱም የሚከተሉትን ማንሳት ይቻላል። 
  1. አባቶች ሰማዕትነትን ለመቀበል ዝግጁ ያለመሆን፦  ቤተ ክርስቲያን እንዳስተማረችን ሰማዕትነት የደም ብቻ አይደለም። ለቤተ ክርስቲያን በተለያየ መልኩ ሰማዕትነት መቀበል እንደሚያስፈልግ እኒሁ ዛሬ ሰማዕትነት ለመቀበል ዝግጁ ያልሆኑት አባቶች አስተምረውናል። ገና በፍራቻ ሥጋዊ ድሎታችን ሊነካብን ይችላል በማለት ለቤተ ክርስቲያን አንድነት መቆም ተስኗቸዋል ብሎ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። ምናልባት የተለያየ ምክንያት ሲያቀርቡ ይሰማል፤ ነገር ግን ምንም ይሁን ምን የቤተ ክርስቲያንን አንድነትና ሰላም ሊነካ የሚችል ምክንያት በምዕመናን ዘንድ ተቀባይነት እንደማይኖረው በውጭም በውስጥም ያሉ አባቶች እንዲረዱልን እንፈልጋለን። የአባቶች ምክንያት ሰማዕትነት ለመቀበል ዝግጁ ያለመሆንና ድፍረት ማጣት ቤተ ክርስቲያን ለ21 ዓመታት ተለያይታ ዛሬም ነገም ወደፊትም በልዩነት እንድትቀጥል ፍርዳቸውን ለማጽናት ምክንያት እየደረደሩ ይገኛሉ። እኔም እንደ አንድ ምዕመን  የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ያገባኛል ምክንያታችሁን ተው፣ ለቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት ስትሉ ሰማዕትነትን ተቀበሉ፣ አላውያን ነገስታትን አትፍሩ ለቤተ ክርስቲያን ዋጋ ክፈሉ እንዲህ ካደረጋችሁ እኛም ከእናተ ጋር ነን ሰማያዊ ዋጋችሁ እንደተጠበቀ ሁኖ።
  2. በምዕመናን መካከል አንድነት አለመኖር፦  በእኛ በምዕመናን ዘንድ ትልቁ ችግርና በሽታ በመካከላችን አንድነትና መተማመን አለመኖሩ ነው። ይህ ችግር ደግሞ በቤተ ክርስቲያን ላይ የተከሰተውን ትልቅ ፈተና በህብረትና በአንድነት ለመወጣት መሰናክል ሆኖብናል። ማን እንደዘራብን እግዚአብሔር ይወቀውና ዘረኝነቱና ፖለቲካው በመካከላችን ነግሶብን የቤተ ክርስቲያንን ችግር ከወሬ የዘለለ ሥራ እንዳንሰራ እንቅፋት ከሆነብን ዘመናት ተቆጥረዋል። በመካከላችን አንድነት ቢኖር ኑሮ በአባቶች በኩል ድክመት ሲኖር በቀላሉ ልንደግፋቸው በቻልን ነበር። ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ያገባናል ይመለከተናል ካልን ሌሎች ልዩነቶችን ትተን ለቤተ ክርስቲያን በአንድነት በመቆም ከገባችበት ችግር ልንታደጋትና ልንቆምላት ይገባል።
  3. በውጭ የሚኖሩ ምዕመናንና በአገር ውስጥ ላሉ ችግሩ እኩል ስሜት አለመኖሩ፦ ምንም እንኳ ለ21 አመት የዘለቀውን የቤተ ክርስቲያን የታሪክ ጠባሳ በትንሹም ቢሆን የማያውቅ የለም ብሎ መናገር ቢከብድም በውጭና በአገር ውስጥ ያለን ሁላችንም እኩል ግንዛቤ ስለሌለን ለችግሩም መፍትሔ ለመፈለግ እኩል ተነሳሽነት የለንም። በተለይ በውጭው አለም የምንኖር ምዕመናን የመጀመሪያ ግንባር ቀደም የችግሩ ቀማሽ በመሆናችን ለዕርቀ ሰላሙ አጽንኦት ሰጠን ድምጻችንን ከፍ አድርገን ስንናገር እንሰማለን። በእርግጥ በአገር ውስጥ ለእርቀ ሰላሙ መሳካት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የሚደክሙ የሉም ለማለት አይደለም በንጽጽር ስናስቀምጠው ነው እንጂ። ያም ይሁን ይህ እርቀ ሰላሙ የቤተ ክርስቲያን የአንድነት ጉዳይ ነውና ሁላችንም ችግሩን እኩል በመገንዘብ ለመፍትሔው መሯሯጥ እጅግ አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም ይህ ወርቃማ እድል ካመለጠን ሌላ ጊዜ ለማግኘት ምናልባት የማናውቀው ብዙ አስርት አመታት ሊፈጅብን ይችላልና።
  4. የመንግሥት ጣልቃ ገብነት፦ እዚህ ላይ ግን ብዙ መናገር አልፈልግም ምክንያቱም በቤተ ክርስቲያን የታሪክ ጉዞ ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ነጻ ሁና በራሷ የተመራችበት የታሪክ አጋጣሚ የለምና። ዛሬም ያለው መንግሥት ስልጣን ከያዘባት ከመጀመራይቱ ቀን ጀምሮ እስከ አሁኗ ስዓት ድረስ በአንድም በሌላም መንገድ እጁን ከቤተ ክርስቲያን ላይ አላወረደም። በመጀመሪያ ለቤተ ክርስቲያን መለያየትና መከፋፈል መንስኤ እንደሆነ ሁሉ ለእርቀ ሰላሙ እንቅፋት መሆኑም በተለያየ ጊዜ የምናያቸውና የምንሰማቸው ነገሮች ማረጋገጫዎች ናቸው። ሌላውን እንተወውና የክቡር ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊርጊስ ደብዳቤ ከበቂ በላይ ማስረጃችን ነው። ስለዚህ እኛ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ያገባናል የምንል ሰዎች በአገኘነው አጋጣሚ ሁሉ "መንግሥት ሆይ ከቤተ ክርስቲያን ላይ እጅህን አንሳ" ልንለው ይገባል።
  5. የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ዝምታ፦ አንዳንዴ  በግሌ አባታችን ግን የት ናቸው? የሚል ጥያቄ ይፈጠርብኛል። ለመሆኑ የአባታችን ዝምታ እስከ መቼ ነው? ምናልባት እኮ መፍትሔው ከእርሳቸው ዘንድ ሊኖር ይችላል የሚል ግምት አለኝ። እስኪ ከሌላ ሰው በስማ በለው ከምንሰማው ይልቅ በራስዎ አንደበት ይንገሩን? ምን ደረሰብዎት? እንዴት ነበር? ሁኔታውን በአጭርና በግልፅ ቁንቋ ይንገሩንና ምዕመኑ አንድ ሁኖ ወደ እውነቱ በህብረት እንዝመት። ወይም ለቤተ ክርስቲያን አንድነትና ሰላም ሲሉ መቀበል ያለብዎትን ሰማዕትነት በጸጋ ይቀበሉና ቤተ ክርስቲያንን አንድ ያድርጉ፤ የ21 ዓመት ዝምታዎት ይብቃ።

  የሰላም አምላክ እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን ሰላምን ያድልልን፡ አሜን።

Thursday, November 22, 2012

Ethiopia


Ethiopia ; Amharicኢትዮጵያ?, officially known as the Federal Democratic Republic of Ethiopia, is a country located in the Horn of Africa, and is the most populous landlocked country in the world. It is bordered by Eritrea to the north,Djibouti and Somalia to the east, Sudan and South Sudan to the west, and Kenya to the south. Ethiopia is the second-most populous nation on the African continent, with over 84,320,000 inhabitants, and the tenth largest by area, occupying 1,100,000 km2. Its capital, Addis Ababa, is known as "the political capital of Africa."
Ethiopia is one of the oldest sites of human existence known to scientists. It may be the region from which Homo sapiens first set out for theMiddle East and points beyond. Ethiopia was a monarchy for most of its history until the last dynasty of Haile Selassie ended in 1974, and theEthiopian dynasty traces its roots to the 2nd century BC. Alongside Rome, Persia, China and India, the Kingdom of Aksum was one of the great world powers of the 3rd century and the first major empire in the world to officially adopt Christianity as a state religion in the 4th century. During the Scramble for Africa, Ethiopia was the only African country beside Liberia that retained its sovereignty as a recognized independent country, and was one of only four African members of the League of Nations. Ethiopia then became a founding member of the UN. When other African nations received their independence following World War II, many of them adopted the colors of Ethiopia's flag, and Addis Ababa became the location of several global organizations focused on Africa. Ethiopia is one of the founding members of the Non-Aligned MovementG-77and the Organisation of African Unity. Addis Ababa is currently the headquarters of the African Union, the Pan African Chamber of Commerce,UNECA and the African Standby Force.
The ancient Ge'ez script is widely used in Ethiopia. The Ethiopian calendar is seven to eight years behind the Gregorian calendar. The country is amultilingual and multiethnic society of around 80 groups, with the two largest being the Oromo and the Amhara, both of which speak Afro-Asiatic languages. The majority of the population is Christian while a third of it is Muslim. Ethiopia is the site of the first Hijra in Islamic history and the oldest Muslim settlement in Africa at Negash. A substantial population of Ethiopian Jews resided in Ethiopia until the 1980s. The country is also the spiritual homeland of the Rastafari movement. There are 9 UNESCO World Heritage Sites in Ethiopia.
Despite being the major source of the Nile, Ethiopia underwent a series of famines in the 1980s, exacerbated by adverse geopolitics and civil wars. The country has begun to recover, and it now has the biggest economy by GDP in East Africa and Central Africa. Ethiopia follows a federal republic political system and EPRDF has been the ruling party since 1991.

Source 
Wikipedia

Monday, November 19, 2012

ጾመ ነብያት/ጾመ ድኅነት/የገና ጾም


ይህ ጾም ከ7ቱ የቤተክርስትያናችን የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ ነው። ይህን ጾም በዋናነት ነብያት  የጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መውረድ፣ መወለድ በትንቢት መነጸር እየተመለከቱ የጾሙት ታላቅ ጾም ስለሆነ ጾመ ነብያት ተባለ። ጾመ ድኅነት መባሉም መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ/የአዳም እዳ በደል/ ጠፍቶ ድኅነት ስለተገኘበት ነው። እንዲሁም ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም አምላክን በመሀጸኔ ተሸክሜ ልጾም ልጸልይ ይገባኛል ብላ ለ40ቀን እስከ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ድረስ የጾመችው ጾም ገና ጾም ተባለ። ስለዚህም ይህ ጾም ስለጌታችን መውረድ፣ የአምላክ ሰው መሆንን/መወለዱን/ የምንረዳበት ጾም ነው። ጾሙም ከህዳር 15 እስከ ጌታችን ልደት ድረስ እንዲጾም ቅድስት ቤተክርስትያናችን በስርዓት ደንግጋ አስቀምጣልናለች።

ለምን ጾሙን ከህዳር 15 ቀን ጀመርን?

ስንክሣር ዘህዳር፤ “ አመ ዐስሩ ወሃምስቱ ለሓዳር በዛቲ ዕለት ጥንተ ጾሙ ስብከተ ጌና ልደቱ ለእግዚእነ ዘሠሩ ክርስትያን ያዕቆባውያን ዘግብፅ ሳህሉ ወምህረቱ የሃሉ ምስሌነ ለዓለም” ህዳር 15 ቀን  የግብፅ ክርስትያን ያዕቆባውያን እንደሰሩት ይህ ዕለት የልደት ጾም መጀመሪያ ነው ማለት ነው። ደግሞም
ፍትሐ ነገስት አንቀጽ  13 ገጽ 218 እና 219፡ ”ወውቱ ጾመ ዘይቀድም እምልደት ወጥንተ ዚአሁ መንፈቀ ህዳር”  የልደት ጾም የሚጀምረው ከህዳር 15 ነው ማለት ነው።

ጾሙ ለምን ከ40 ቀን በለጠ?

አንደኛ፦ ሐዋርያው ፊልጶስ ህዳር 16 ቀን በሰማዕትነት አሳርፈውት ሊያቃጥሉት ሲሉ መልአከ እግዚአብሔር ሰወረው። ደቀመዛሙርቶቹ/ ተማሪዎቹ/ ከዕለቱ ጀምረው ሶስት ቀን እንደጾሙ በ18 ሰጣቸውና ቀበሩት ስለዚ 3 ቀን ጾመ ፊልጶስ ተብሎ ተጨመረ ማለትም ህዳር 16፣17 እና 18።
 ሁለተኛው፦ ህዳር 15 ደግሞ ልደት ሁልጊዜ ረዕቡና አርብ ባይውልም አበው ስርዓት ከሰሩ አይልዋወጥምና አንድም ደግሞ አንዴ ሲጾም አንዴ ሲበላ እንዳይረሳ  ብለው ሁልጊዜም ጾሙ ከህዳር 15 እንዲጀመር አድርገው አፀኑት። ስለዚህ  አንድ ቀን በጾሙ ጨምረው ጥንታውያን ክርስትያኖች በዕግብፅ ከህዳር 15 ቀን ጀምረው ጾሙት። ለእኛም አርዕያ ሆኑ ስርዓትም ሆኖ ተሰራልን።

       ልደት

የጌታችን የመድኅኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ታህሳስ 29 ቀን ነው። አባቶች በሰሩልን ስርዓት መሰረት ከ4 ዓመት አንድ ጊዜ በዘመነ ዮሐንስ ታህሳስ 28 ቀን ይከበራል። ይህም የሆነበት ዋናው ምክንያት  ልደት የሚውለው ሁልጊዜም  “ዕለተ ምርያ” በዋለችበት ቀን ነው። ዕለተምርያ የምትውለው ምንጊዜም ጳጉሜ 5 ቀን ነው። ጳጉሜ 5 ቀን ሰኞ ቢውል ልደትም መዋል ያለበት ሰኞ ቀን ነው። ይህን በዘመነ ዮሐንስ ስንቆጥረው ዕለተምርያ በዋለችበት የሚውለው ታህሳስ 29 ቀን ሳይሆን ታህሳስ 28 ቀን ስለሚሆን ልደት በዚያ ተወሰነ። ዕለተምርያ ማለት የመድሀኒት ዕለት ማለት እንደሆነ ነብያት ተናግረዋል። በዚህም ዕለት በዋለችበት የዓለም መድሀኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ይወርዳል ይወለዳል እያሉ ትንቢት ስለተናገሩ ነው።  

ጾሙን በሰላም፣ በፍቅር፣ በአንድነት፣ በመተሳሰብ እንድንጾምና ከጾሙ ረድኤት በረከት እንድናገኝ የእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ይሁንልን፤ የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን፡አሜን።