Friday, May 31, 2013

ስለአባይ ምን ተባለ?

                                                                                           በከበደ ካሳ
https://blogger.googleusercontent.com/img/b/R29vZ2xl/AVvXsEj9wbVH3TqueRjGM3LyUpt3jQf2OavsAU0D0Unns3zubiU2JSQAzNnDMH0mM4myVrtf8LneYC6FurAXKUKjLG4p75zsxhM65wMVlYJG8O811fYb03HLA5tmNM3QcQQJE6Y1VbZwOJgJBNY/s1600/%E1%8A%95%E1%8C%8C.jpg
ኢትዮጵያ ግንቦት 20/2005 የአባይ ወንዝን የተፈጥሮ አቅጣጫ መቀየሯ የአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንና ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ ሀገራት መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል፡፡ ዋናው ጉዳይ ምሽት ላይ አልጀዚራ በኢንሳይድ ስቶሪ /inside story/ ፕሮግራሙ ከኢትዮጵያ አቶ በረከት ስምዖንን፤ ከግብፅ ላማ ኤል ሃሎንና ከእንግሊዝ ሊዮ ፓስካልን በማስገባት ዉይይት ያደረገበት ነው፡፡ በዚህ ላይ በኋላ እመለስበታለሁ፡፡ አሁን ግን መገናኛ ብዙሃን፤ ግብፅና ሱዳን ምን አሉ የሚለዉን እንመልከት፡፡

በጉዳዩ ላይ ሰፊ ዘገባ የሰጠው አህራም የተባለዉ የግብፅ ድረ-ገፅ ነው፡፡ ቢቢሲ፤ አልጀዚራና ዋሽንግተን ፖስትም እንዲሁ፡፡ ሁሉም ታዋቂ መገናኛ ብዙሃን በተለያየ መጠን ለጉዳዩ ሽፋን ሰጥተውታል ማለት ይቻላል፡፡ ከብዛታቸውና ከምንጫቸው ተመሳሳይነት አንፃር የያንዳንዱን ዘገባ አቅጣጫ ከማየት ይልቅ በዚህ ጉዳይ ላይ በስፋት አስተያየታቸውን ወደሰጡት ግለሰቦች አትኩሬአለሁ፡፡
ከላይ ከቁንጮው እንነሳ፡፡ ማለቴ ከግብፅ መንግስት አቋም፡፡ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ያወጣው መግለጫ አሁን በአባይ ወንዝ ላይ እየተካሄደ ያለው ግንባታ በውሃ መጠኑ ላይ መቀነስን ሊያስከትል የሚችል እንዳልሆነ የሚገልፅ ነው፡፡ በአባይ ላይ የሚገነባ ማንኛውም ፕሮጀክት ከመጀመሩ በፊት የወንዙን አቅጣጫ በማስቀየር ቦታውን ለግንባታ ምቹ ማድረግን ይጠይቃል ብሏል መግለጫው፡፡ ስለሆነም ከተለመደው ውጭ የሆነ አዲስ ነገር የለም የሚል ይመስላል፡፡
የግብፅ ካቢኔም በጉዳዩ ላይ ትናንት በዝግ ከመከረ በኋላ ባወጣት ቁራጭ መግለጫ የግድቡ ግንባታ ተጀመረ ማለት ግብፅ እውቅና ሰጥታዋለች ማለት አይደለም ብሏል፡፡ ያም ሆኖ የግብፅና ሱዳን የውሃ ድርሻን የማይቀንስ እስከሆነ ድረስ ማንኛዉንም የልማት ፕሮጀክት እደግፋለሁ ብሏል ካቢኔው፡፡ ካቢኔው ጨምሮ እንደገለፀው ለማንኛውም የሶስትዮሽ ኮሚቴውን የጥናት ሪፖርት ይፋ መሆን እንደሚጠብቅ ገልጧል፡፡ ሪፖርቱን ተከትሎ የሚይዛቸዉን አቋሞች /የሚወስዳቸዉን እርምጃዎች/ ከወዲሁ እንዳዘጋጀም ካቢኔው ጠቁሟል፡፡ ምን እንደሆኑ ፍንጭ ከመስጠት ቢቆጠብም፡፡ በዝች መግለጫ መጨረሻ የገባችዉ አረፍተ ነገር ደግሞ “ግብፅና ሱዳን በአንድ ልብ ሆነን በጉዳዩ ላይ ተባብረን እየሰራን ነዉ” ትላለች፡፡ ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ እያደላች ነው የሚለዉን ዘገባ ለማጣጣል የገባች አረፍተ ነገር ሳትሆን አትቀርም፡፡
አሁን ዘግይቶ እንደተረዳሁት ደግሞ ዛሬ ግንቦት 22/2005 ፕሬዝዳንት ሙርሲ ከተመረጡ ሚንስትሮች ጋር በዚሁ ጉዳይ ላይ ለመምከር ቀጠሮ ይዘዋል፡፡
የሃገሪቱ የሹራ ምክር ቤት ደግሞ በመጭው እሁድ በዚሁ ጉዳይ ላይ ለመምከር የአስቸኳይ ስብሰባ ቀን ቆርጧል፡፡ በስብሰባው የውጭ ጉዳይና የደህንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎችን ጨምሮ 6 ኮሚቴዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡
እኔ እንዳገኘሁት መረጃ ከሆነ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሃገሪቱ ያሉትን የኢትዮጵያ አምባሳደር ሞሃሙድ ድሪርን አስጠርቶ በጉዳዩ ላይ ቃላቸዉን ተቀብሏቸዋል፡፡ ምስኪን! ምን ብለዉ ይሆን? የሚኒስቴሩ የስራ ሃላፊዎች ከበው በጥያቄ ሲያዋክቧቸው፡፡ እንደ መረጃው ሰዎቹ በኢትዮጵያ ዉሳኔ መከፋታቸዉን ለአምባሳደሩ ገልፀውላቸዋል፡፡
ከአባይ ወንዝ የፍሰት አቅጣጫ ማስቀየር ጋር በተያያዘ ስማቸው በተደጋጋሚ የተነሳዉ የግብፅ ውሃና መስኖ ልማት ሚንስትሩ ሞሃመድ ባሃ ኢልዲን ናቸው፡፡ እሳቸዉ የንግግራቸው መጀመሪያ ያደረጉት ግብፅ በጥቅሟ ላይ የሚመጣን ማንኛውንም አይነት ፕሮጀክት እንደማትደግፍ መግለፅ ነው፡፡ ይህ አቋማቸው እንዳለ ሆኖ የወንዙ የፍሰት አቅጣጫ መቀየሩ ግን ለግብፅ ምንም ጉዳት እንደሌለው ለጋዜጠኞች አረጋግጠዋል፡፡ “የተለመደ የግንባታ ሂደት መገለጫ ብቻ ነዉ” ብለውታል፡፡

የአንድ ሃገር ሚኒስትር ከዚህ በላይ ሊሉት የሚችሉት በጎ ነገር ሊኖር አይችልም፡፡ የሃራቸውን ጥቅም የሚጎዳ ነገር ካለ እሱን መቃወም አለባቸው፤ ከሚጠቅማቸው ጋር ደግሞ መተባበር፡፡ እሳቸው ያሉትም ይህንኑ ነው፡፡ አሁን በግብፅ ላይ የተደቀነ አደጋ የለም፤ የጋራ ኮሚቴው ሪፖርት እስከሚወጣ እንጠብቃለን ነው ያሉት፡፡
እኝህ ሰው በቅርቡ በሃገሪቱ በተደረገው የስልጣን ሽግሽግ ባሉበት እንዲቆዩ ሲደረጉ እንኳን ደስ አለዎት በማለቴ የተረቡኝ እንደነበሩ አስታውሳለሁ፡፡ ሰውየው ምንም ያህል ትችት ቢሰነዘርባቸውም ስለኢትዮጵያ ያላቸውን በጎ እይታ በአደባባይ ከመግለፅ ያልተቆጠቡ ናቸው፡፡
ሌላዉ በዚህ ጉዳይ በንቃት የተሳተፉት በኢትዮጵያ የግብፅ አምባሳደር ሞሃመድ እድሪስ ናቸው፡፡ የህዳሴው ግድብ ግብፅ የግዷንም ቢሆን ልትቀበለው የሚገባ የማይቀር ክስተት /reality/ ነው ብለዋል፡፡ የግብፅ የድርድር ግብ መሆን ያለበትም ግድቡን ማስቆም ሳይሆን ሁለቱም ወገኖች ተጠቃሚ በሚሆኑበት መንገድ ላይ ሊሆን እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡ “የአስዋን ግድብ ለኛ አንደሚያስፈልገን ሁሉ የህዳሴዉ ግድብም ለኢትዮጵያውያን ብሄራዊ ሃብታቸው ነዉ” ሲሉ ነው እዉነታውን ፊት ለፊት ለመጋፈጥ የቆረጡት፡፡ አምባሳደሩ አሁን ኢትዮጵያ ያደረገችው ነገር ዱብ እዳ ሳይሆን ካለፈው ህዳር ጀምሮ የምናውቀው ነው ብለዋል፡፡
በሁሉም መድረኮቻችን ኢትዮጵያ በኛ ላይ ጉዳት እንደማታስከትል ደጋግማ አረጋግጣልናለች፤ እኛም ይህንኑ አምነን ተቀብለናል ያሉት አምባሳደሩ ግብፅ ሶስቱም ወገኖች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አሰራር እየፈለገች መሆኗን ተናግረዋል፡፡

እኔ የነዚህን ባለስልጣናት ንግግር በአወንታዊ መልኩ ነው ያየሁት፡፡ ምክንያቱም ቢያንስ ኢትዮጵያ እነሱን የመጉዳት ሃሳብ እንደሌላት መረዳታቸዉን ገልፀውልናል፡፡ የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ቀስ በቀስ ቅቡል እየሆነ መምጣቱን አመላካች አስተያየት ነው፡፡
ሆኖም የሀገሪቱና የአለምአቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘገባ አሉታዊ ነው፡፡ መገናኛ ብዙሃኑ ከግድቡ ጋር ያሉ አወንታዊ ጎኖችን ዘወር ብለዉ እንኳን ሳያዩ ሊያስከትል ይችላል ብለዉ ባሰቡት ተፅዕኖ ላይ ብቻ ነዉ ያተኮሩት፡፡
ባለስልጣኖቹ ከተናገሩት ውስጥ ሲመርጡ እንኳን ይህንኑ ፍላጎታቸውን የሚያሟላላቸዉን ንግግር ብቻ እንጅ በመቻቻልና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮሩትን አገላለፆች በተደጋጋሚ ዘለዋቸዋል፡፡ ለምሳሌ ያክል ሞሃመድ ባሃ ኢልዲን ግብፅ በጥቅሟ ላይ የሚመጣን ማንኛውንም አይነት ፕሮጀክት እንደማትደግፍ መግለፃቸውን ሲያራግቡ በግብፅ ላይ የተደቀነ አደጋ የለም ማለታቸውን ግን ብዙዎቹ አድበስብሰውት አልፈዋል፡፡
ሌላው የሚጠበቅ ግን ቢሆንም መታወቅ ያለበት የግብፅ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አቋም ነዉ፡፡ ፓርቲዎቹ ይህንን ጉዳይ ለፖለቲካ ጥቅም ማግኛ ሲጠቀሙበት ተስተውለዋል፡፡ እነሱ እንደ ጠንካራና ለግብፅ ህዝብ የቆሙ፤ ሙስሊም ብራዘርሁድ የሚመራው መንግስት ደግሞ እንደ ልፍስፍስና የህዝቡን ጥቅም አሳልፎ የሰጠ አድርገው አሳይተዋል፡፡ የናሽናል ሳልቬሽን ፍሮንቱ ኤል ባራዲ በቅርብ ሰዓት በግል ቲዊቱ የሲና በረሃና ኢትዮጵያ መተላለቅን የሚያስከትሉ አደገኛ የቀውስ ምንጭ እንደሆኑ ተንብየዋል፡፡ ይችን ነገር ከኛ ሃገር ተቃዋሚዎች የኮረጇት ሳትሆን አትቀርም፡፡ በነገራችን ላይ የኛዎቹ እስካሁን ድምፃቸዉ አልተሰማም፡፡ የአባይ መንገዱን መቀየር አልሞቃቸውም፤ አልበረዳቸውም፡፡
ይህ በንዲህ እንዳለ የሱዳኑ የውሃ ሃብትና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር ሞሃመድ ሃሰን በጉዳይ ላይ ለመምከር ወደ ካይሮ ሄደዋል፡፡ እዛ እንደደረሱም ከግብፁ አቻቸው ጋር ተመካክረዋል፡፡ ምን እንደዶለቱ ግን እስካሁን ወሬ አላገኘሁም፡፡ ወደ ሱዳን ከገባሁ አይቀር በዚሁ የሱዳን ሁኔታ እንመልከት፡፡
በግብፅ የሱዳኑ አምባሳደር ከማል ሃሰን የአባይ ወንዝ አቅጣጫ የመቀየር ዜና አስደንጋጭ እንደሆነና ሱዳንና ግብፅ የአረብ ሊግን ጣልቃ ገብነት ሊጠይቁ እንደሚችሉ ተናግረዋል በሚል ትናንት በርካታ መገናኛ ብዙሃን ተቀባብለውት ነበር፡፡ ሆኖም ከምሽት ጀምሮ በአንዳንድ የግብፅ ጋዜጦችና በሱዳኑ ሱዳን ትሪቡን ድረ ገፅ የወጣ ዘገባ አምባሳደሩ ይህንን ማለታቸውን የሚያስተባብል ነው፡፡

የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እኛ እንዲህ አይነት ንግግር ካፋችን አልወጣም ብሏል፡፡ ኢትዮጵያ እያደረገች ያለችው ነገር በሱዳን ላይ ምንም ጉዳት እንደሌለው አረጋግጠናል፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ሁላችንም ተጠቃሚ በምንሆንበት ነገር ላይ ከኢትዮጵያም ሆነ ግብፅ ጋር ለመተባበር ዝግጁ ነን ሲል አቋሙን አሳውቋል፡፡
እስኪ አሁን ደግሞ ትናንት ምሽት በአልጀዚራ ስለተላለፈዉ ፕሮግራም ላንሳ፡፡ በኢንሳይድ ስቶሪ ፕሮግራም ላይ ከአዲስ አበባ የመንግስት ኮሚዪንኬሽን ሚኒስትሩ አቶ በረከት ስምዖን፤ ከካይሮ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዋ ላማ ኤል ሃሎና ከለንደን ደግሞ ደራሲዋ ሊዮ ፓስካል ቀርበዋል፡፡
የፕሮግራሙ አዘጋጅ ገና ሲጀምር የህዳሴውን ግድብ በግብፅ ህልውና ላይ የተደቀነ አደጋ አድርጎ ነው ያቀረበው፡፡ የግብፅ ህዝብ በ2050 /በነሱ አቆጣጠር/ 150 ሚሊዮን ስለሚደርስ ግብፅ ተጨማሪ 21 ቢሊዮን ኪዉቢክ ሜትር ውሃ ያስፈልጋታል፤ ግድቡ ግን እንኳን ይህን እድል ሊሰጣት 18 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ያሳጣታል ሲል በመደምደም ይነሳል፡፡ የሃይል ማመንጨት አቅሟንና የግብርና ምርት መጠኗንም ይቀንሰዋል፤ በዚህም ሚሊዮኖች ለረሃብ ይጋለጣሉ ይላል ጋዜጠኛዉ፡፡

አቶ በረከት በሰጡት ምላሽ ታዲያ እንደማስበው የኢትዮጵያ ፍላጎት በግብፅም ሆነ ሱዳን ላይ ይህን ያህል ጭንቅ መፍጠር ሳይሆን የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት ነው አሉ፡፡
ጋዜጠኛዉ “ፍላጎታችሁ ጉዳት ማድረስ ላይሆን ይችላል ግን ሂደቱ ይህን ጣጣ ሊያመጣ ይችላል” ሲል አቋረጣቸው፡፡ በረከትም ሂደቱ የሚያስከትለዉ እንደውም የተሻለ የዉሃ መጠን ነዉ፡፡ ምክንያቱም እኛ በአካባቢያችን የምናከናውነው የተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤ ስራ የከርሰ ምድር ዉሃ መጠንን የሚያሳድግ ነው ሲሉ ተከራክረዋል፡፡
በዚህ ግዜ ጋዜጠኛው ሊዎ ፓስካልን ግብፅ የሱዳንን መሬት ተጠቅማ በኢትዮጵያ ላይ የሃይል እርምጃ ልትወስድ የምትችልበት እድል እንዳለ ጠየቃት፡፡ እርሷም ስትመልስ ግብፅ ይህን ስልት ቀድማም ትጠቀምበት እንደነበር አስታውሳለች፡፡ በተለይም ሶማሊያንና ኤርትራን በመጠቀም ኢትዮጵያን የማዳከም ስልት ትከትል እንደነበር አውስታለች፡፡ አሁን ግን የኢትዮጵያ ጡንቻ በአካባቢው እየፈረጠመ መሆኑን ታነሳና የጦርነት አማራጭ ለግብፅ አዋጭ እንዳልሆነ በተዘዋዋሪ አስረድታለች፡፡
ጋዜጠኛው ውሃን እንደጦር መሳሪያ አድርጎ ማየቱ ያላስደሰታቸዉ አቶ በረከት “እኛ ዉሃ ያጣላናል ብለን አናስብም፡፡ ይህ አንተ የምትለዉም ግዜ ያለፈበት ተረት ነዉ” ብለውታል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ወጭውን ብቻዋን ትሸፍነው እንጅ ጥቅሙ የሁሉም ሀገሮች ነው፡፡ ግብፅም ሆነች ሱዳን በበጋ ወራት ሳይቀር ወጥነትና ብዛት ያለው ዉሃ ሊያገኙ እንደሚችሉ የተከዜው ግድብ ለሰሜን ምስራቅ የሱዳን አካባቢዎች ያስገኘዉን ጥቅም በአብነት በማንሳት አብራርተዋል፡፡
በቅኝ ግዛት ወቅት የተፈረሙ ስምምነቶች ኢትዮጵያን ያገለሉ እንደሆኑና ይህንን በመቀየር ኢትዮጵያም ሆነች ሌሎቹ ሃገራት በጋራ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አሰራር መዘርጋት እንደሚገባ ተከራካሪዎቹ አንስተዋል፡፡ ፓስካ “ኢትዮጵያ የድርሻዋን ካልተጠቀመችማ ለውሃው /ለወንዙ/ ደህንነት ለምን ትጨነቃለች?” ስትል መልሳ ጠይቃለች፡፡ ኤል ሃሎ በበኩሏ የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ንግግርን በማስታወስ ግድቡ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይሆን የአካባቢው ሃብት እንደሆነ አሳይታለች፡፡
በአጠቃላይ ሲታይ ውይይቱ መግባባት የሰፈነበት ነበር፡፡ ሆኖም ከኢትዮጵያው ሚኒስትር በስተቀር ሌሎቹ ጉዳዩ በቀጥታ የማይመለከታቸውና የመወሰን ስልጣን የሌላቸዉ መሆኑ የውይይቱን ፋይዳ ያሳንሰዋል፡፡ ውይይቱ በሶስቱ ሃገራት ከፍተኛ ባለስልጣኖች መካከል ቢሆን ይሻል ነበር፡፡ ነገር ግን ሱዳንና ግብፅ በአሁኑ ሰዓት /ቢያንስ የገምጋሚው ቡድን ሪፖርት ይፋ እስኪሆን/ ለመነጋገር ዝግጁ የሆኑ አይመስልም፡፡

Renaissance Dam of Abay Vs Egypt

Pope Tawadros II: Church not asked to arbitrate in Nile crisis


Coptic Pope Tawadros II has said that the president’s office did not ask him to address the Ethiopian Church to resolve the Nile water crisis after Ethiopia began to divert the course of the Blue Nile on Tuesday.

Egypt fears this measure will reduce its water supply.

In a phone conversation with Anadolu News Agency, Tawadros said that he has not received a phone call from President Mohamed Morsy or any other government official regarding the issue.

Some in the Egyptian media have said that Morsy asked Tawadros to capitalize on the historical relations between the Egyptian and Ethiopian Churches and that he had agreed and had invited the Ethiopian Pope to an urgent visit to Egypt.
Meanwhile, a source from the papal headquarters said that, "The pope will not hesitate to help resolve the Nile water crisis if asked," and added that Tawadros will meet with Ethiopian Church leader Abune Mathias in Cairo on 19 July and that they may discuss the issue then.
In statements to Anadolu, the same source emphasized that "the Ethiopian Church has no role in the Ethiopian decision-making process; it can give advice only."
The Ethiopian Church has long-standing relations with the Egyptian Church, but it cannot actually intervene to stop the construction of the dam, the source added.
The last meeting between the former Ethiopian pope and the late Pope Shenouda III in November 2012 did not tackle the Nile Basin crisis, added the source.

Former Egyptian commander: Striking Ethiopia dam 'impossible'

General Mohamed Ali Bilal, commander of Egyptian forces during the Gulf war, said that it is “impossible” to strike the Ethiopian Renaissance Dam because such a decision would be issuing a challenge to the entire world.
Bilal told al-Arabiya satellite channel on Wednesday that such an attack would bring Egypt into conflict with those countries, such as China and Israel, whose citizens are involved in the construction of the dam. Egypt is not in a position to stand up to all those countries, he added.
He also said that, when the US launched Desert Storm and invaded Kuwait, it did so under the auspices of the UN. Besides, he added, there seems to be international consensus that Ethiopia has the right to build the dam.
He emphasized that the US had planned its construction and that Israel is providing technical support. In Bilal’s view, the only way to tackle the crisis is to persuade the US to intervene on Egypt's behalf and convince the Ethiopians to mitigate the impact construction of the dam will have.
Major General Ahmed Abdel Halim, a security and strategic expert, said that a diplomatic solution is the best way of handling this issue, while adding that striking the dam would not bring the aspired results.
He also said that, as a last resort, Egypt could present its case to the International Court of Justice, the Security Council, and the International Criminal Court.
 
Listen   Al Jazeera Inside Story - Bereket Simon discusses the impact of Abay Dam on Egypt and Sudan

My question is that, what are the expecting from Government, Politicians/Opposition parties/, Non Government organizations, Diasporas and every Ethiopian regarding this issue???

Saturday, May 25, 2013

መነኰሳትን አይቻለሁ

 ከእለታት አንድ ቀን ጻድቁ አባታችን አባ መቃርዮስ ከግብጽ አስቄጥስ ወደ ኒጥርያ ተራራ አባ ፖምቦን ፈልጎ ሄደ። አባ ፖምብም "አባታችን እስኪ ለመነኰሳቱ የሆነ ቃል በላቸው" አለው። አባ መቃርዮስም "እኔ ራሴ ገና መነኩሴ አልሆንኩም ነገር ግን መነኰሳትን አይቻለው" አለ። ያየውንም እንዲህ በማለት ነገራቸው፦ "ብቻዬን በበኣቴ ውስጥ ተቀምጨ እያለሁ ባለሁበት በርሃ ውስጥ ማን እንዳለ ለማወቅ በማሰብ ወደ በርሃ እንድሄድ ሃሳቤ አስቸገረኝ። እኔም ይህ ሃሳብ ከአጋንንት የመጣ ጸብአ ፍልሰት/ከብኣቴ ሊያስወጣኝ/ እንዳይሆን ብዬ በመስጋት ለአምስት ዓመት ያህል ከዚያ ከሚያስቸግረኝ ሃሳብ ጋር ስታገል ቆየሁ። ነገር ግንነገሩ ከእግዚአብሔር እንደሆነ ስረዳ ወደ ውስጠኛው በርሃ ለመሄድ ከበኣቴ ወጣሁ። አርባ ቀናት ተጉዤ ወደውስጠኛው በርሃ ደርሼ ጸሎት ካደረስኩ በኋላ ስኳዝ ከአንድ ወንዝ አጠገብ ደረስኩ።
ከዚያም ከመካከሉ ደሴት አለውና ጥቂት ውኃ አገኘሁ። የበርሃ አራዊቱም ወደዚያ በመምጣት ይጠጣሉ። ውኃ ሊጠጡ ከሚመጡት አራዊት መካከልም ሁለት እርቃናቸውን የሆኑ፣ ሰውነታቸው በጣም የከሳና ፀጉራቸው የረዘመ፣ የእጅና የእግር ጥፍራቸው እንደ እንስሳት በጣም የረዘመ ሰዎች አየሁና ታላቅ ፍርሃትን ፈራሁ፤ ሰውነቴም ተንቀጠቀጠ፣ እነርሱ መናፍስት ናቸው ብዬ ነበርና። ነገር ግን እኔን ባዩኝ ጊዜ ተንቀሳቀሱ፣ እነርሱም በስሜ ጠርተው እንዲህም አሉኝ።
  • "መቃሪ ሆይ! አትፍራ እኛም እንደ አንተ ሰዎች ነን። ወደዚህ እንዴት መጣህ? ከዚህስ ምን ትሰራለህ?" አሉኝ።
  • እኔም የፈለግኩትን ከእኔ ያላራቀ እግዚአብሔር እውነተኛ ቅዱሳን የሆናችሁትን አያችሁ ዘንድ ፈቀደልኝ። በረከታቸው ትድረሰኝ አልኩና ቀርቤ ዳሰስኳቸው፣ መንፈስ እንዳይሆኑ ብዬ ሰግቼ ነበርና። እኔም በበርሃ የሚኖሩ ቅዱሳንእንደሆኑ ባወቅሁ ጊዜ ወደ እርሳቸው ቀርቤ እጅ ነሣኋቸው፣ እነርሱም ባረኩኝ፣ ብዙ ነገርም ነገሩኝ። በዚህ በርሃ ከመጣን ጀምሮ ከአንተ በቀር ከአንድም ሰው ጋር ተገናኝተን አናውቅም አሉኝ። 
  • እኔም "ከየት መጣችሁ? ከዚህ በርሃስ እንዴት መጣችሁ?" አልኳቸው።
  • እነርሱም እንዲህ አሉኝ፦ የመጣነው ከገዳም ነው፣ ሁለታችንም ተስማምተን ከዚህ ከመጣን አርባ አመታችን ነው። አንዳችን ግብጻዊ ስንሆን ሌላችን ሊቢያዊ ነን" አሉኝ። " ዓለም እንዴት ናት?? ዝናብ በወቅቱ ይዘንባልን ብለው ጠየቁኝ።
  • እኔም የጠየቁኝን መለስኩላቸውና እንዴት መነኩሴ መሆን እችላለሁ? ብዬ ጠየቅኋቸው።
  • እነርሱም "በዓለም ያሉትን ነገሮች በሙሉ ካላቆምክ መነኩሴ መሆን አትችልም" አሉኝ።
  • እኔም እኔ ደካማ ነኝ፣ እናንተ እንደምትሠሩት ልሰራ አልችልም አልኳቸው።
  • እነርሱም "እንደኛ መሆን ካልቻልክ በበኣትህ ተቀመጥና ስለ ኃጢያትህ  አልቅስ" አሉኝ።
  • እኔም ክረምት ሲመጣ አይበርዳችሁምን? በጋስ ሲሆን ሙቀቱ ሰውነታችሁን አያቃጥለውምን? አልኳቸው። 
  • እነርሱም "ይህን ዓይነት አኗኗር እግዚአብሔር ለእኛ አዘጋጀልን፣ ክረምት ሲመጣ አይበርደንም፣ በጋ ሲሆንም ሙቀቱ አይ ጎዳንም" አሉኝ።
ከዚህም የተነሣ አባ መቃርዮስ "እኔ መነኰሴ አይቼ መጣሁ እንጂ ገና መነኰሴ አልሆንኩም" አለ። ዛሬ ስንቶች ናቸው የአባታችን የአባ መቃርስ ትህትና፣ ትዕግስት፣ ማስተዋል፣ ራስን መግዛትና ጸጋቸውን መለየት ተስኗቸው/ረስተው ያልሆኑትንና ያልነበሩበትን ሲሰብኩና ሲናገሩ የምንሰማቸው? ስንቶች ናቸው የተቀደሰውን ገዳማዊ ሕይወት ሲያራክሱ የምንሰማቸው? የቀደሙት አባቶቻችን ግን የመንፈስ ፍሬን ገንዘብ አድርገው፣ የሆኑትን እንኳ በትህትና እራሳቸውን ዝቅ አድርገው እኛ ኃጢያተኛ ነን፣ አልበቃንም፣ መንፈስን መለየት ይገባናል እያሉ ነበር ይችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያስረከቡን። እኛም ዛሬ እንደ አባታችን አይቻለሁ እንጂ እኔ አይደለሁም እያልን ለመሆን ትጋቱንና ብርታቱን ያድለን ዘንድ አምላከ ቅዱስ መቃርስን  በጸሎት እንማጸነው።

የጻድቁ አባታችን ጸሎቱ፣ ረድኤቱና አማላጅነቱ አይለየን፡ አሜን።

Wednesday, May 22, 2013

የባህርዳር ሀዘን

ሰሞኑን ባህር ዳር ሀዘን በሀዘን ተደራርቦባታል። ምንም እንኳ ሀዘኑ በተለያየ መልኩ ቢከሰትም አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተደጋጋሚ አደጋ በመከሰቱ ሀዘኗን እጥፍ ድርብ አድርጎባታል።
 1, ግንቦት 4 /2005 ዓም  በአንድ  ፌደራል  ፖሊስ   በመንግሥት  መገናኛ 12  ሰዎችን፤  በኢሳትና  በተለያዩ ድህረ ገጾች ደግሞ ከ 16 እስከ 18 ሰወችን መግደሉ ባህርዳርን በሀዘን  ትገኛለች።

 የኢሳት ምንጭ/ESAT

2, ግንቦት 12/2005 ዓም ደግሞ በልጆቿ መሞት እንበዋን ሳታብስ ሌላ ተጨማሪ ልብ የሚሰብር ሀዘን፤
ከምእራብ ጎጃም ዞን ሰሜን አቸፈር ወረዳ ልዩ ስሙ ቁንዝላ ተነስቶ ወደ ሰሜን ጎንደር ጣቁሳ ወረዳ ደልጊ ከተማ 101 መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረው ጀልባ ግንቦት 12/2005 ከቀኑ 10:30 በጋጠመው ድንገተኛ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
ከአደጋው ከ90 በላይ ሰዎች ህይወት ሊተርፍ መቻሉንና እስከ አሁን የጠፉ ሰዎችን የማፈላለግ ስራም እየቀጠለ መሆኑን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡/ምንጭ፣ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን/
3, ትናንት ምሽት ማለትም በ13/2005 ዓም በባህርዳር ከተማ ውስጥ የሚገኝ የጅምላ ንግድ አካፋፋይ ድርጅት/ጅንአድ መቃጠሉን የተለያዩ  መገናኛ ብዙሀንና ድህረ ገጾች e እየገለጹ ይገኛሉ።
የኢሳት ምንጭ/ESAT 

እግዚአብሔር አምላክ ለሞቱት ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን፤ለአዘኑት መጽናናትንና መረጋጋትን ይስጥልን፡ አሜን!

Wednesday, May 15, 2013

የፌድራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሃይማኖት ተቋማትን ለመመዝገብ ያወጣው ረቂቅ መመሪያ

አንብቡና የራሳችሁን አስተያየት ስጡበት

ይህን መመሪያ ስመለከት በ2000 ዓም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሃይማኖት ጉዳይ የወጣውን መመሪያ እንዳስታውስ አደረገኝ። በዚያን ወቅት ማንኛውም ሃይማኖትን ሊገልጹ የሚችሉ ነገሮችን የሚቃወም ስለነበር  የከፍተኛ ት/ት ተቋማት  ተማሪዎችን በእጅጉ ያሳዘነ፣ ያስቆጣና እምነትንም የሚፃረር  እንደነበር አስታውሳለሁ። 






Sunday, May 5, 2013

ሁለቱን በጣምራ/በአንድነት ማስኬድ አይቻልም?

በሁሉም ማለት ይቻላል የሃይማኖት አስተምሮ ሥጋዊና መንፈሳዊ ሥራዎችን ሁለቱን በጣምራ ማስኬድ እንደሚቻል በሚያስተምሩት የአስተምሮ ዘይቢያቸው ይሰብካሉ። በተለይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እንደ ቀደምትነቷ ለዚህ በር ከፋችም አይነተኛ ምሳሌም ናት። "ሥጋ ካለነፍስ፡ ነፍስ ካለ ሥጋ አትቆምም"፤ ሁለቱ ተያያዥና ተደጋጋፊ ናቸው፤ አንዱ ካለአንዱ መቆምና ሥራቸውን ማከናወን እንደማይችሉ አስፍታና አሙልታ ታስተምራላች።
ምንም እንኳ መንፈሳዊነቱ ጥያቄ ውስጥ ቢገባም ብዙ አገሮች ይህንን መርህ ተከትለው ተግባራዊ ሲያደርጉ ይታያሉ፤ለስኬትም በቅተዋል። ይህንንም አብነት አድርገው የበለጸጉ አገሮችም ሆነ በማደግ ላይ ያሉ አገሮች ተያያዥ ነገሮችን ዛሬም በጣምራ/በአንድነት ለማስኬድ ሲሞክሩ ይታያሉ። በሙከራቸውም እድገትን፣ ብልጽግናን፣ ሰባዊ ርኅራሄንና እኩልነትን በመጠኑም ቢሆን ህዝባቸው ተጠቃሚ እንዲሆን አድርገዋል።
ወደ አገራችን ኢትዮጵያ ስንመለከት ግን ሌሎች በርካታ ነገሮችን ትተን እጅግ ለሰው ልጅ መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን እንኳ በአንድነት ለማስኬድ አልተቻለም፤ ለማድረግም ሙካራ ሲደረግ ጎልቶ አይታይም። ለዚህ ችግር ሁላችንም በትንሹም ቢሆን ከተጠያቂነት ባናመልጥም በዋናነት ግን አገሪቱን እያስተዳደረ ያለው መንግሥት ትልቁን ድርሻ ይወስዳል።

የአገራችን መንግሥት ልማታዊና ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ነኝ ብሎ ከነገረን አመታትን አስቆጥሯል። በእውነት ሁኖ ከተገኘና ለመሆን ጥረት የሚያደርግ ከሆነ በእርግጥም መልካምና የሚደገፍ ሃሳብ ነው። በእርግጥ አቶ መለስ በህይወት በነበሩበት ጊዜ ልማትና ዲሞክራሲ ምንም ግንኙነት እንደሌላቸው ተናግረው ነበር። ፓርቲያቸውም የእርሳቸውን ቃል ተግባራዊ ለማድረግ ሌት ተቀን እየሰራ እንደሆነ ምስክር መሆን ይቻላል። በልማት ስም ነጻነት ሲገፈፍ፣ በልማት ስም የእምነት ተቋማት ሲፈርሱ፣ በልማት ስም ታሪካዊ ቦታዎች ታሪካቸው ሲጠፋ፣ በልማት ስም ሰዎች ከቦታቸው ከንብረታቸ  ሲፈናቀሉ እያየን እየተመለከትን ነው። እኔ የዝወትር ጥያቄዬ ግን  ሁለቱን በጣምራ ማስኬድ አይቻልም? የሚለው ነው። ዶ/ር ዘላለም ተክሉ፡ አቶ መለስ"ዲሞ ክራሲና ልማት ምንም ግንኙነት የላቸውም" ብለው በተናገሩት ላይ ትችታቸውን በጥናታዊ ጽሁፍ እንዲ አቅርበዋል።
የዲሞክራሲ ጥንታዊ ትርጉም “ የህዝብ ሃይል” ወይም “ የህዝብ አስተዳደር” ሲሆን መሰረቱም ሁለት የግሪክ ቃላቶች ዴሞስ(demos)  “ህዝብ” እና ክራቶስ (kratos) “ሃይል” ውህደት ነው:: የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት በነበሩት አብረሃም ሊንከን አተረጓጐምም መሰረት ደግሞ ዲሞክራሲ ማለት በህዝብ የተመረጠና ለህዝብ የቆመ የህዝብ መንግስት ማለት ነው:: በዚህ ዓይነት ስርዓት ውስጥ የተመረጡ መሪዎች ቀጥተኛ ተጠሪነታቸው (accountability) ለህዝቡ ሲሆን የሚሰጡት አገልግሎትም በህዝቡ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ብቻ እንደሆነ ይገለጻል:: ዘመናዊው የዲሞክራሲ ምንነት በቀደምቶቹ ትርጉሞች ላይ የዳበረ ሲሆን የሰው ልጅ መሰረታዊና ፖለቲካዊ መብቶች የማክበር፣ በህዝቦች መካከል የሰፈነ እኩልነት፣ ነጻና ፍትሃዊ የመምረጥና የመመረጥ መብት ያለው፣ ሃሳብን በነጻነት መግለጽ የሚፈቅድ፣ እንዲሁም ከማንኛውም ተጽዕኖ ነጻ የሆነ የፍትህ ሥርዓትንና ነጻ ፕሬስ ያካተተ ተቋምም እንደሆነ ይታወቃል::

የኢኮኖሚ ልማትም በጣም የሰፋ፣ ከጊዜ ጊዜ ተለዋዋጭና አከረካሪ ትርጓሜ የያዘ ንድፈ ሃሳብ ነው:: ልማት ቀደም ባሉ ጊዜያት ሲተረጎም የሰው ልጅ ያለውን የጉልበት፣ የካፒታልና የዕውቀት አቅም አሻሽሎ ምርታማነትን በማሳደግ በሚያገኘው የተሻለ የነፍስ ወከፍ ገቢ ከድህነት የተላቀቀና የተመቻቸ ኑሮ መኖር መቻል ነበር:: የኖቤል ተሸላሚው ኢኮኖሚስት አማርቲያ ሴን እንደሚያስረዳው ደግሞ በ1980ዎቹና 90ዎቹ በኋላ የልማት ትርጉም እየሰፋ መጥቶ ከኢኮኖሚ ጠቀሜታ በተጨማሪ የሰብዓዊና የፖለቲካ ነጻነት መብቶችን፣ ስፋት ያላቸው ማህበራዊ ዕድሎችን፣ የአመራር ግልጽነትና የደህንነት ዋስትና እንዲያካትት ተደርጎ እንዲሰራበት ተደርጓል:: የሰብዓዊ ተሟጋች ድርጅቶች ደግሞ የልማት ትርጓሜ ከላይ ከተዘረዘሩት በተጨማሪ የሰፋ የህብረተሰብ ተሳትፎና የመሪዎች ግልጽነት (transparency) መያዝ እንዳለበት አበክረው ያሳስባሉ:: ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በስፋት ተቀባይነት ያገኘውና በብዙ ሃገራት፣ ዓለም አቀፍ የልማትና የፋይናንስ ተቋማት እየተሰራበት ያለው ደግሞ የሌላውን የኖቤል ተሸላሚ ኢኮኖሚስት ጆሴፍ ስቲግሊትዝ ትንታኔን መሰረት በማድረግ የጎለበተው አስተሳሰብ ሲሆን በዚህ ትርጓሜ መሰረት ልማት ማለት ከኢኮኖሚ ዕድገት ባሻገር የሰው ልጅ ከማህይምነት የሚላቀቅበት፣ ለረጅም ዕድሜ ሊኖር የሚችልበትና ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል የሚጎናጸፍበት ደረጃ እንደሆነ ታምኖበታል::

ስለዚህ የሃገራችን መንግሥትም በስም ከመነገድና ህብረተሰቡን ግራ ከማጋባት ይልቅ እነዚህ ሁለቱን በጥምረት ማስኬድ ይችል ነበር። እርግጥ ነው በአንድ ጊዜ ተግባራዊ ማድረግ ከማሰብ በላይ እጅግ አዳጋች ነው፤ ሆኖም ግን በሂደት መድረስ የማንችልበት ምንም ምክንያት የለም። ምክንያቱም ይህን በጥምረት ከሚያስኬዱ ሃገራት በአቅምም በሰው ኃይልም የተሻልን እንጂ ያነስን አይደለንምና።
ዲሞክራሲንና ልማትን፤ ነጻነትንና ልማትን፣ እኩልነትንና ልማትን፣ ሰላም ፍቅርንና ልማትን፣ የህብረተሰቡን ፍላጎትና ልማትን፣ የእምነት ተቋማት ሳያፈርሱ ልማትን በጣምራ ማስኬድ አይቻልም? መልሱ ይቻላል ነው። ብዙዎች እንደሚስማሙት ነጻነት ካለ ልማት አለ፣እድገት አለ፣ ብልጽግና አለ፣ መከባበርና ግልጽ ውይይት በህብረተሰቡ ዘንድ ይኖራል። ስለዚህ ከሁሉም በፊት ለነጻነትና ለዲሞክራሲ ቅድሚያ በመስጠት ሁለቱን በጣምራ ብናስኬዳቸው መልካም ይሆናል የሚል ሃሳብ አለኝ።
የእያንዳንዳችን ድርሻ፦ በጉልበታችን፣በገንዘባችን፣በሃሳባችን/በእውቀታችን እና በአገኘነው አጋጣሚ ተጠቅመን ከዘረኝነት ርቀን መንግሥት መልካም ነገሮችን በጥምረት እንዲያስኬድ ድጋፍና አቅጣጫ ማሳየቱ የውዴታ ግዴታችን መሆኑን አውቀን ብንሰራ ለውጥ ልናመጣ እንችላለን።

መልካም የትንሣኤ በዓል!
የዘወትር ምኞቴ የነጻነት ትንሣኤ ለኢትዮጵያ.................

Friday, May 3, 2013

ዕለተ ዓርብ/ስቅለት


ሐዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስ «አውቀውስ ቢሆን የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት» /1ቆሮ.1-18/፡፡ እንዳለ ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ያለበደል ያለጥፋት ንጹሕና ጻድቅ የሆነውን ጌታ የሰቀሉበት ዕለት ነው፡፡ ዕለቱም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ሁሉ መድኃኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልእልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የምናስብበት ታላቅ ቀን ነው፡፡ /ማቴ.27-35-75/፡፡ በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ አለ፡፡ እነርሱ ግን እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ አሉ፡፡ ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሔደና ታንቆ ሞተ፡፡ የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አልተፈቀደም አሉ፡፡ ተማክረውም የሸክላ ሠሪ መሬት ለእንግዶች መቃብር ገዙበት፡፡ ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተባለ፡፡ /ማቴ.27-3-9/
የሰው ልጆች በዘር ኃጢአት /ቁራኝነት/ ይኖሩበት የነበረው የጨለማ ሕይወት ያከተመበት ፍጹም ድኅነት ያገኙባት ታላቅ ዕለት ናት፡፡ ክርስቲያኖች ሁልጊዜም ዕለተ ዓርብ ሲመጣ ሕማሙን ስቅለቱን ሞቱን የሚያስቡበት ጊዜ ነው፡፡ በሮማውያን ሕግና ሥርዓት መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት የሕይወት መቅጫ አርማ ሆኖ ሳለ ለእኛ የዲያብሎስ ድል መንሻ ስላደረገው በስቅለቱና በሞቱም ሕይወትን ስለአገኘን በዚህም ምክንያት መልካሙ ዓርብ በመባል እንደሚታወቅ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ያትታሉ፡፡
በመስቀል ላይ ሳለ 7 ነገሮችን ተናገረ/7ቱ "አጽርሐ መስቀል" በመባል ይታወቃሉ። እነሱም፦
" አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ" ማቴ 17፦46
" አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው" ሉቃ 23፦34
" ዛሬ በገነት ከኔ ጋር እንድትኖር በእውነት እነግርሀለሁ" ሉቃ 23፦4
" አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ" ሉቃ 23፦ 46
" እነሆ ልጅሽ እነኋት እናትህ" ዮሐ 19፦26
" ተጠማሁ" ዮሐ 19፦28
" ሁሉ ተፈጸመ " ዮሐ 19፦ 30
ጌታ ሁሉ ተፈጸመ ብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ስጋው በራሱፈቃድ ከለየ በኋላ አምላክነቱን ለመግለፅ የታዩ ተአምራት የሚከተሉት ናቸው፤

በሰማይ፤ /ማቴ 24፦29 እና 27፦45/
1. ፀሐይ ጨለመች
2. ጨረቃ ደም ሆነች
3. ከዋክብት ረገፉ

በምድር፤/ማቴ 27፦51_53/
1. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይእስከ ታች ተቀደደ
2. ምድር ተናወጠች
3. መቃብሮች ተከፈቱ
4. ሙታን ተነሱ


ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ ክንዋኔዎች በሰሙነ ሕማማት
በዐቢይ ጾም ከሠርክ ሆሣዕና ጀምሮ እስከ ትንሣኤ ሌሊት ዕለታት የሚገኙበት ሳምንታት ሰሙነ ሕማማት ይባላሉ፡፡ ዕለታቱም የዓመተ ፍዳ፣ የዓመተ ኩነኔ መታሰቢያ ናቸው፡፡ በእነዚህ ዕለታት ውስጥ የተለያዩ ትውፊታዊ እና ሃይማኖታዊ ክንዋኔዎች አሉ፡፡ ከነዚህ ክንዋኔዎች ውስጥ አለ መሳሳም፣ አክፍሎት፣ ቄጤማ ማሰር፣ ጥብጣብ፣ ጉልባን እና ሕጽበተ እግር ይገኙበታል፡፡ ስለእነዚህ ክንዋኔዎች በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስላለው ትውፊታዊ አፈጻጸም መዛግብት አገላብጠን እና በኢትዮጵያ ኣርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሊቃውንት ጉባኤ አባል የሆኑትን ሊቀ ካህሃት ክንፈ ገብርኤል አልታዬን አነጋግረን እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡
አለመሳሳም
በሰሙነ ሕማማት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች መስቀል እንደማይሳለሙት ሁሉ መጨባበጥ፣ መሳሳምና የትከሻ ሰላምታ መለዋወጠን አይፈጽሙም፡፡ ሰላምታ የማንለዋወጥበት ምክንያት፣ አይሁድ ጌታን ለመስቀል ሰኞ እና ማክሰኞ መከሩ አልሠመረላቸውም፡፡ ምክራቸው የተፈጸመው ረቡዕ ነው፡፡
ስለዚህ አይሁድ አያንሾካሾኩ “እንስቀለው… አንግደለው” ብለው ይማከሩ ነበር፡፡ ያነን ለማስታወስ ሰላምታ አንለዋወጥም፡፡ መስቀልም አንሳለምም፡፡ ሳምንቱ የክፋት ምክር የተመከረበት እንጂ የፍቅርና የደስታ ሰላምታ የታየበት ባለመሆኑ ይህንን በማሰብ ሰላምታ አንለዋወጥም፡፡
ይሁዳ ጌታን በጠላቶቹ ለማስያዝ “እኔ የምስመው እርሱ ነው፤ ያዙት” ብሎ በሰላምታው ምልክት ሰጣቸው ይህ ሰላምታ አምሐ ቅድሳት አይደለም፤ ተንኮል የተሞላበት እንጂ፡፡ የዲያቢሎስም ሰላምታ ተመሳሳይ ነው፡፡ ሔዋንን “ሰላም ለኪ” ብሎ ነው ያታለላት፣ የዲያቢሎስ እና የይሁዳ ሰላምታ ሰይጣናዊ ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን ወቅትና ሁኔታ ለማሰብ በሰሙነ ሕማማት ሰላምታ ልውውጥ የለም፡፡ ዛሬ እየተስተዋለ ያለው ይኸው ሰላምታ ያለመለዋወጥ ሁኔታ ሥርወ መሠረቱ ይህ ነው፡፡ ከጥንት ጀምሮ እዚህ ትውልድ ላይ ደርሷል ይቀጥላልም፡፡

ሕጽበተ እግር
ጌታ በፍጹም ትሕትና የደቀ መዛሙርቱን እግር ያጠበበት፣ ከሐዋርያት ጋር ግብር የገባበትና የክርስትና ሕይወት ማሕተም የሆነውን ምሥጢረ ቁርባን ያከናወነበት ዕለት ነው ጸሎተ ሐሙስ፡፡
ሕጽበተ እግር ጌታችን በዚህ ዕለት “አናንተ ለወንድማችሁ አንዲህ አድርጉ” ለማለት የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠቡ ምክንያት የተሰጠ ምሳሌ ነው፡፡ ይህም የሚያሳየው “አኔ ለአናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም፣ መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም፤ ይህን ብታውቁ ብታደርጉትም ብፁዓን ናቸሁ” /ዮሐ.13÷16-17/ በማለት ትሕትናውን አሳይቷል፡፡
ጌታ በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግር ሲያጥብ “እኔ መምህራችሁ ስሆን እግራችሁን ካጠብኳችሁ አርአያዬን ሰጥቻችኋለሁ፤ እናንተም የወንድማችሁን እግር ታጥቡ ዘንድ ይገባል፡፡ ነገር ግን ከእናንተ አንዱ ለሞት አሳልፎ ይሰጠኛል” አለ፡፡ ደቀ መዛሙርቱም “ማን ይሆን?” አሉ፡፡ ጌታም “ኅብስት ቆርሼ፣ ከወጡ አጥቅሼ የምሰጠው እርሱ ነው” አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ደነገጡ፡፡ ይሁዳን ማመልከቱ ደነገጡ፡፡ ይሁደን ማመልከቱ ነበር፤ ለጊዜው አልገባቸውም፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን የሐዋርያቱን እግር በማጠብ ትሕትናን ካስተማራቸው በኋላ፤ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሰጣቸው፤ የኦሪትን መሥዋዕት የሻረው እና መሥዋዕተ ሐዲስን የሠራው በዚሁ ዕለት ነው፡፡
በዚህ ሃይማኖታዊ መነሻነትም በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ድርጊቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ፡- በወሎና በጎንደር ከጉልባን በተጨማሪ በተለይ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት ብቻ የሚጋገር የተለየ ዳቦ አለ፡፡ ይህ ልዩ ዳቦ በወሎ “ትኩሴ” በጎንደር ደግሞ “ሙጌራ” ይባላል፡፡ ይህ ዳቦ ጌታ ለሐዋርያት የሰጣቸው ኅብስት አምሳያ ነው ተብሎ ስለሚታሰብ ከዚህ ቀን ውጪ በሌላ ጊዜ አይጋገርም፡፡ በመሆኑም ሰው ሁሉ ዳቦውን ለመብላት የሚጠባበቀው በታላቅ ጉጉት ነው፡፡ አልፎ አልፎ ግን ሃይማኖታዊ ሥርዓት በሚከበርባቸው እንደ ማኅበርና ሰንበቴ በመሳሰሉት መንፈሳዊና ማኅበራዊ ትውፊቶች የሚቀርብበት ጊዜ አለ፡፡
በትግራይ በዕለተ ስቅለት ከተለመደው የጾምና የስግደት ሥርዓት በተጨማሪ የሚከናወኑ ድርጊቶች አሉ፡፡ በዕለቱ ለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት መታሰቢያ ሲባል ወንዶች ልጆች በሙሉ ፀጉራቸውን እንዲላጩ ይደረጋል፡፡ ያን ቀን ያልተላጨ ልጅ “ኃጢአት ይሆንበታል” ስለሚባል ሳይላጭ የሚውል ልጅ የለም። ልጃገረዶች በበኩላቸው በዛፍ ላይ ገመድ በማሰር ዥዋዥዌ ይጫወታሉ፡፡ ይህንንም የሚያደርጉት የጌታን እንግልትና መስቀል ለማዘከር ነው ይባላል፡፡
እነሆ ይህንን ዕለት በማስታወስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሐዶ ቤተ ክርስቲያን ከሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ እስከ ቀሳውስት ያሉት አባቶች በያሉበት አጥቢያ /ደብር/ በመገኘት በመዓርግ የሚያንሷቸውን የካህናት፣ ዲያቆናት እና የምእመናንን እግር ያጥባሉ፤ የሚያጥቡትም የወይራ እና የወይን ቅጠል በመዘፍዘፍ ነው፡፡

አክፍሎት
በሰሙነ ሕማማት ዕለተ ዓርብ ከስግደት በኋላ ምእመናን በየቤታቸው ጥቂት ነገር ለቁመተ ሥጋ ቀምሰው እስከ እሑድ /የትንሣኤ ሰዓት/ ይሰነብታሉ፡፡ ይህ አክፍሎት ይባላል፡፡ ብዙው ምዕመን ከዓርብ ጀምሮ የሚያከፍል ሲሆን አንዳንዶች ግን ከሐሙስ ጀምረው ያከፍላሉ፡፡ ይህም እመቤታችን፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ የጌታን ትንሣኤ ሳናይ እህል ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሣኤ መቆየታቸውን ተከትሎ የመጣ ትውፊት ነው፡፡
ይህንን ትውፊት አስመልክቶ ሄሬኔዎስ፣ አውሳብዮስ የተባሉ ጸሐፍት፤ ሐዋርያት በሰሙነ ሕማማት ከደረቅ ዳቦ አና ከትንሽ ውኃ በቀር እንደማይመገቡ እና ከሐሙስ ጀምረው እንደሚያከፍሉ ጽፈዋል፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ሐዋርያት ሌሎቹንም እንዲያከፍሉ እንዳሳሰቡና ከሐሙስ ጀምሮ ያልተቻለው ቢያንስ ከዓርብ ጀምሮ እንዲያከፍል ማዘዛቸውን ጽፈዋል፡፡ የእኛ ቤተ ክርስቲያን ትምህርትም ይኸው ነው፡፡ ቅዳሜ ይበላል ማለት ግን ቅዳሴው ሌሊት ስለሆነ በልቶ ማስቀደስ ነውና በልቶ እንደመቁረብ ይቆጠራል፡፡

ጉልባን እና ቄጤማ
ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚባላ ንፍሮ ነው፡፡ የጉልባን ትውፊት እስራኤላውያን ከግብፅ ተሰደው በሚወጡበት ጊዜ በችኮላ ስለነበር፤ አቡክተው ጋግረው መብላት ያለመቻላቸውን ሁኔታ ያመለክታል፡፡ ያን ጊዜ ያልቦካውን ሊጥ እየጋገሩ ቂጣ መብላት፤ ንፍሮም ቀቅለው ስንቅ መያዝ ተግባራቸው ነበር፡፡ ይህን ለማሰብ በሰሙነ ሕማማት ቂጣና ጉልባን በማዘጋጀት በዓሉ ይታሰባል፡፡
በጸሎተ ሐሙስ ይህንን መሠረት በማድረግ የሚዘጋጀው ጉልባን አንዲህም ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል፡፡ ጨው ውኃ የሚያስጠማ በመሆኑ የጌታን መጠማት ያስታውሳል፡፡ ይህ ትውፊታዊ ሥርዓት ከእስራኤላውያን የመጣ ሲሆን በኢትዮጵያም አብዛኛዎቹ የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ሥርዓቱ ዛሬም ይከበራል፡፡
ጥብጣብ
በሰሙነ ሕማማት ዕለተ ዓርብ የስቅለቱ መታሰቢያ ነው፡፡ ምእመናኑ በሰሙነ ሕማማት የሠሩትን ይናዘዛሉ፡፡ ካህናቱም በወይራ ቅጠል ትከሻቸወን እየጠበጠቡ ቀን ከሰገዱት ስግደት በተጨማሪ ሌላ ስግደት ያዟቸዋል፡፡ ጥብጠባው የተግሳፅ ምሳሌ ነው፡፡ ጥብጣብ የሚደረግለት ሰው በሕማማቱ ወቅት የፈጸመው በደል ወይንም ኃጢአት ካለ ይህንኑ በመናገር የስግደቱ ቁጥር ከፍ እንዲል ይደረጋል፡፡
ይህ በስቅለት ቀን የሚፈጸም ሥነ ሥርዓት ሲሆን፤ ጠብጣቤ ማለት ቸብ ቸብ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ሕዝበ ክርስቲያኑ በዕለተ ስቅለት ሲሰግድ ሲጸልይ፣ ሲያነብ ከዋለ በኋላ ሰርሆተ ሕዝብ /የሕዝብ መሰነባበቻ/ ከመሆኑ በፊት፤ በወይራ ቅጠል እያንዳንዱን ምእመን ጀርባ ቸብ ቸብ መደረጉ፣ የጌታን ግርፋት ያስታውሳል፡፡

ቀጤማ
በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለ ዓዋዲ/ እየመቱ “ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ” የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቀጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቀጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ የደፉበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡
በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቀጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጭሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡

                                    ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ እግዚአብሔር በሰላም!
(ምንጭ፦ ስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት መጋቢት 2002/ከማኅበረ ቅዱሳን ድኅረ ገጽ )

Thursday, May 2, 2013

ዕለተ ሐሙስ

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዕለት ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑን ለመግለጥ እና ለአርአያነት ጸሐፍት ፈሪሳውያን የአይሁድ ካህናት መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ጸሎተ ሐሙስ በመባል ይታወቃል፡፡ ትሕትና ፍቅር መታዘዝ እንዲሁም የአገልግሎትን ትርጉም ለማስረዳትና ለማስገንዘብ የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠቡ ሕጽበተ ሐሙስ በመባልም እንደሚጠራ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይናገራሉ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስም  «እግራቸውንም አጥቦ ልብሱንም አንሥቶ ዳግመኛ ተቀመጠ እንዲህም አላቸው ያደረግሁላችሁን ታስተውሉታላችሁን?... እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ እናንተ ደግሞ እርስ በእርሳችሁ ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል ሲል ተናግሯል፡፡ /ዮሐ.13-12-20/፡፡

ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ስለ እናንተ የሚፈስ ደሜ ነው ከእርሱ ጠጡ በማለት ምሥጢረ ቁርባንን የመሠረተበት ወይም ራሱ ምስጢረ ቁርባንን የጀመረበት ቀን በመሆኑ የምስጢር ቀን ተብሎ ይጠራል፡፡ ይኸውም የሰው ልጆች ሥጋውንና ደሙን ተቀብለን ከእርሱ ጋር አንድነትና ኅብረት እንዲኖረን ጥንተ ጠላት ዲለብሎስንም ፍጹም ድል ነሥተን ሰማያዊት ርስት መንግሥተ ሰማያትን እንድንወርስ ለማስቻል ነው፡፡ /ማቴ.26-26-29/፡፡ የሚለምን ሥጋን የተዋሐደው አምላክ ፍፁም ሰውም መሆኑን ለመግለፅና ለአርያነት በጌቴ ሰማኒ ጸሎት አደረገ። ዕለቱ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ስለሆነ የነፃነት ሐሙስም ይባላል።

አይሁድ ጌታችንን ለመያዝ በእነርሱ ጥበብና ፍላጐት ቀስ ብለው መጥተው የያዙበት ቀን ስለሆነ በዚህ ዕለት በለሆሳስ /ብዙ የድምጽ ጩኸት ሳይሰማ/ የቅዳሴ ሥርዓት ይፈጸማል፡፡ ስለሆነም መላው ሕዝበ ክርስቲያን በዚህ የሕጽበት፣ የምስጢር፣ የጸሎት ቀን በተባለው በዚህ ዕለት በንስሓ ታጥበው ሥጋ ወደሙ እንዲቀበሉ ቤተ ክርስቲያን በአጽንኦት ታስተምራለች፡፡

Wednesday, May 1, 2013

ሰሙነ ሕማማት(ዘረቡዕ)

          በመምህር ኃይለማርያም ላቀው/በማኅበረ ቅዱሳን መካነ ድር ላይ የወጣ
 
በቅዱስ ማቴዎስና በቅዱስ ማርቆስ አዘጋገብ መሠረት ሦስት ነገሮች በዕለተ ረቡዕ ተደርገዋል፤ እነርሱም የሚከተሉት ናቸው፡፡

1. የካህናት አለቆች÷ የሕዝብ ሽማግሌዎችና ጸሐፍት ፈሪሳውያን በጌታችን ላይ ተማክረዋል፤
2. ጌታችን በስምዖን ዘለምጽ ቤት ሳለ አንዲት የተጸጸተች ሴት ሽቱ ቀብታዋለች፡፡
3. ከዳተኛው ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ለመስጠት ከጸሐፍት ፈሪሳውያንና ከካህናት አለቆች ዘንድ 30 ብር ተመዝኖለታል፡፡
የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሹማምንት በጌታችን ላይ ይሙት በቃ ለመወሰን የሰበሰቡት ሸንጐ “ሲኒሃ ድርየም” ይባላል፡፡ በዚህ ሸንጐ ላይ በአብዛኛው የተሰየሙት ሰዱቃውያን ሲሆኑ የተቀሩቱ ደግሞ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ነበሩ፡፡ ሸንጐው በአጠቃላይ 72 አባላት የነበሩት ሲሆን የሚመራው በሊቀ ካህናቱ ቀያፋ ነበር፡፡
በዕለቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት ይዘው እንደ ሚገድሉት መክረዋል፡፡ ከዳተኛው ይሁዳ በጸሐፍት ፈሪሳውያንና በካህናት አለቆች ዘንድ ይጉላላ የነበረውን ጥላቻ ያውቁ ስለነበር “ምን ልትሰጡኝ ትወዳላችሁ እኔም አሳልፌ እሰጣችኋለሁ” በማለት ጌታችን አሳልፎ ሊሰጣቸው እንደሚችል ተዋውሏል፡፡ የአስቆሮቱ ይሁዳ ጌታችን ያስተምር በነበረበት ወቅት ከተለያዩ ሰዎች የሚገባውን ገንዘብ ሰብሳቢ /ዐቃቤ ንዋይ/ ነበር፡፡ ከሚሰበሰበው ሙዳየ ምጽዋት ለግል ጥቅሙ እየቀረጠ የማስቀረት የእጅ አመል ነበረበት፡፡ ይሁዳ ፍቅረ ንዋይ እንደሚያጠቃው ድብቅ አመሉ ጎልቶ የወጣው ጌታችን በለምጻሙ በስምዖን ቤት ሳለ አንዲት ሴት ዋጋው ውድ የሆነ ሽቱ በቀባችው ጊዜ ይሁዳ የተቃውሞ ድምፅ ካሰሙት አንዱ ነበር፡፡ “ይህ ሽቱ ተሽጦ ለድሆች ቢሰጥ መልካም ነበር” በማለት ያቀረበው ሐሳብ “አዛኝ መሳይ ቅቤ አንጓች” እንደ ሚባለው ነበር፡፡ ሽቱ ሲሸጥ የሚያገኘው ጥቅም አለ፤ ሽቶ ከፈሰሰ የሚተርፈው የለም፡፡ ይህ በመሆኑ ተቆርቋሪ መስሎ ያቀረበው ሐሳብ ተቀባይነት ስላጣ ማኩረፊያ ያገኘ መስሎት በቀጥታ ከካህናት አለቆች ዘንድ ሄዶ ተዋዋለ፡፡ ብር 30 ተመዘነለት፡፡ ይህ አሳዛኝ ታሪክ በሦስቱ ወንጌላት ውስጥ በሚከተሉት ጥቅሶች ቀጽፎ እናገኛለን፡፡ ማቴ.26÷3-16፤ ማር.14÷1-11፤ ሉቃ.22÷1-6 ይመልከቱ፡፡
የአስቆሮቱ ይሁዳ እንደ ሌሎች ሐዋርያት ከጌታችን እግር ስር ተምሯል፡፡ በረከተ ኅብስቱን ተመግቧል፡፡ የተለያዩ ገቢረ ተአምራት በጌታችን እጅ ሲደረጉ ሁሉ ተመልክቷል፡፡ ጌታችንም ከሌሎቹ ሁሉ ሳይለየው እግሩን አጥቦታል፤ ከዳተኛው ይሁዳ ግን ለሐዋርያነት የጠራውን ተንበርክኮ እግሩን ያጠበውን ጌታውን አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ “የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል÷ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት እንደ ተባለ፡፡” ማቴ.26÷24፡፡ ሌሎች ሐዋርያት ከጌታችን ዘንድ ፍቅሩን ገንዘብ ሲያደርጉ ይሁዳ ግን እርግማንን ነው ያተረፈው፡፡ “ገንዘብ የኃጢአት ስር ነው” ተብሎ አንደ ተነገረ ይህ የኃጢአት ስር የክርስቲያኖችን ሕይወት ሊያደርቅ ስለሚችል ለገንዘብ ያለን ፍቅር በልኩ ሊሆን ይገባል፡፡ ሰው ይህን ህልም ቢያተርፍ ነፍሱን ከጐዳ ምን ይጠቅመዋል ተብሎ የተነገረውን ቃል ልብ ማለት ጠቃሚ ነው፡፡
ክርስቲያን ነን በማለት የክርስትናውን ስም በመያዝ እምነታቸውን፣ የቆሙበትን ዓላማ በመገንዘብ የሚለውጡ ሰዎች ዛሬም እንደ ይሁዳ ጌታችንን እየሸጡት እንደሆነ ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ ለድሆች መመጽወት ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው፡፡ ዳሩ ግን በድሆች ስም የሰውን ገንዘብ ለግል ጥቅም ማዋል እጅግ የከፋ ኃጢአት ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ለገንዘብ ብለው ድሆችን ለረሃብ ለችግር ባልንጀራቸውን ለመከራ እና ለሞት አሳልፈው ሲሰጡ ምንም አይጸጽታቸውም፡፡ እውነተኛ ክርስቲያኖች ግን ሕይወታችንን ለገንዘብ ፍቅር ሳይሆን ለእምነታችንና ለባልንጀራችን አሳልፈን መስጠት ይኖርብናል፡፡ በፍቅረ ንዋይ ተጠምደን ሰዎችን አሳልፎ በመስጠት ለአይሁዳዊ ሸንጐ ምቹ ሆነን መገኘት እንደሌለብን መገንዘብ አለብን፡፡

                              ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ እግዚአብሔር በሰላም