Sunday, October 26, 2014

ወጣቶች ስለአገራቸው ሰፊ ውይይት አካሄዱ (ኖርዌይ,ኦስሎ)

የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የወጣቶች ክፍል ቅዳሜ ጥቅምት 10/2007 ዓምኦክቶበር 25/2014ለአገር እድገትና ለድሞክራሲ ግንባታ የወጣቶች አስትዋጾ” በሚል ርዕስ ሰፊ ውይይት ከ15:00 እስከ 18:00 ስዓት ተካሄደ።
የመግቢያ ንግግሩ በድርጅቱ ህዝብ ግንኙነት በአቶ አቢ  አማረ የውይይቱን ዓላማና አስፈላጊነት ለተሳታፊው በመግለጽ ወጣቱ ትውልድ ለአገር እገድትና ዲሞክራሲያዊ ግንባታ ያለውን ከፍተኛ አስትዋጾ ሁሉም ተገንዝቦ የወያኔን አስከፊ ስርዓት ለመታገል በዚህ መልኩ  ውይይት መካሄዱ ሊበረታታ የሚችልና ውይይቱም ውጤት ሊያመጣ በሚችል መልኩ እንዲካሄድ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት ይኖርበታል ብለዋል።
በመቀጠልም በክፍሉ ተወካይ በወጣት ይበልጣል ጋሹ ለውይይቱ በሚጠቅም መልኩ የወጣቱን አስፈላጊነትና እንዴት ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ሰፊ ገለጻ ሰጧል። ከገለጸው ሃሳብም መካከል የአንድ አገር ቀጣይነት ያለው እድገት የሚለካው በአላት ሃብትና ንብረት ብቻ ሳይሆን ያንን ተረክቦ በአደራ ለትውልድ ማስተላለፍ የሚችል ትውልዳዊ ትስስር መኖርና ይህንንም እንደ ድልድይ ሆኖ  ከአንዱ ትውልድ ወደቀጣዩ ትውልድ የሚያስተላልፈው ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል እንደሆነ፤ በማንኛውም አገር፣ ጊዜና ዘመን እያንዳንዱ ተተኪ ትውልድ የአገሩ ወራሽ፣ ተተኪና ተረካቢ፣ ጠባቂና ለሚቀጥለውም ትውልድ የማውረስ፣ የማስተላልፍና የማስረከብ ኃላፊነትና ግደታ እንዳለበት፤ ወጣት ለአንድ አገር በሦስቱም ዘርፍ ማለትም በማህበራዊ፣  በምጣኔ ሃብታዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማድረግ እንደሚችል ተረድቶ ወጣቱ ትውልድ በዓላማ፣ በቁርጠኝነት፣ በዕቅድና በመደራጀት  ለአገር እድገት፣ ነጻነት፣ፍትህና ዲሞክራሲ መታገልና ለውጥ ማምጣት እንዳለበት ለውይይት እንደ መነሻ ባቀረበው ሃሳብ ላይ ገልጿል። እንዲሁም የወያኔን አስከፊ፣ ዘረኛና አምባገነናዊ ሥርዓት ለማስገወገድ  ወጣቱ ትውልድ የበኩሉን ሃላፊነት ወስዶ ይህን  ለአገርና ለህዝብ መቆም እንዳለበት በመግለጽ የውይይት ሃሳቦችን አስቀምጦ ስዓቱን ለውይይት ክፍት አድርጓል። ወጣቱንም በሦስት ክፍል ለመክፈል ሞክሯል። እነሱም 1. ወጣትነትን ተጠቅሞ ለአገሩ የሚያስብ የሚጨነቅ፣ አገራዊ ስሜት ያለው፣ የለውጥ ኃይል የሆነ፣ ለነጻነትም የሚታገል፣ለአገር እድገትና ዲሞክራሲ ግንባታ የሚፋጠኑ፤ 2. አገሩን የማያውቅ፣ ማንነቱን የረሳ፣ ማዎቅም የማይፈልግ፣ ለጠቅም ብቻ የሚጓዝ እና 3. በስሜት የሚጋዝ፣ ከነፈሰውና ከሞቀው ጋር የሚጓዝ ዓላማና ግብ የሌለው በማለት ከተናገሩ በኋላ ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ይህን ተገንዝቦ እራሱን ከጥቅምና አድር ባይነት አርቆ ለአገር በሚጠቅም መልኩ እራሱን ማነጽና ማስኬድ እንዳለበት አሳስቧል።
በውይይቱም በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ወጣቱ ለክፉም ለመልካምም የራሱ የሆነ ትልቅ አገራዊ ታሪክ እንዳለው በመግለፅ  ወጣቱ እንዴት መታገልና ለውጥ ማምጣት እንደሚችል ገንቢ አስትያየቶች፣ ምክሮችና አቅጣጫ ተሰጠዋል። ከተነሱትት ሃሳቦች መካከልም በበቂ ሁኔታ መደራጀት፣ በእውቀት እራስን ማብቃት፣ አገራዊ ስሜት መላበስ፣ታሪክን ጠንቅቆ ማዎቅ፣ አንድነት መፍጠር፣ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ስልታዊ እቅድ መከተል፣ አቀራረባችንን እና ትኩረታችን መለየት፣ ቀጣይነት ያላቸው የውይይት መድረኮችን ማዘጋጀት እና ክፍሉን ማደራጀት ከተነሱት አበይት ሃሳቦች መካከል ነበሩ። በተጨማሪም ክፍሉ ከሌሎች የወጣት ህብረት ጋር ግንኙነት በመፍጠር ልምድና ተሞክሮ  በመለዋወጥ ወጣቱን ይበልጥ ማንቃትና ፖለቲካዊ አድማሱን ማስፋትና የወያኔን ጨቋን መንግሥት ሊታገል የሚችልበትን አቅጣጫ ማሳየትና መንደፍ ተገቢ መሆኑን አጽንኦት ተሰጦበታል። 
በአጠቃላይ  ወጣቶች ለአገር እድገት፣ ለነጻነት፣ ለሰባዊ መብት፣ ለፍትህና ለዲሞክራሲ ግንባታ የወጣቱ አስትዋጾ ከፍተኛ መሆኑን ተረድቶ በሁለገብ ትግል ወያኔን/ ሕወሓትን ለማስወገድ የበኩሉን ኃላፊነትና ግዴታ መወጣት እንዳለበት በሥፋት ተገልጿል። ክፍሉም የተሰጠውን አስተያየት እና ምክር ተግባራዊ ለማድረግ የድርሻውን እንደሚወጣና ወያኔን ለመታገል በማነኛም መልኩ ዝግጁ እንደሆነ አሳውቋል።
በመጨረሻም  አቶ ልዑል ታደሰ ውይይቱ መልካምና ሂደቱም ጥሩና የተሳካ መሆኑን ገልጸው ለተሰብሳው ክፍሉን በሁሉም አቅጣጫ መደገፍና ማጠናከር ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የሚጠበቅ መሆኑን አስረድተዋል።  እንዲህ አይነት ውይይት በተለይ ለወጣቱ አስፈላጊና አስተማሪ ስለሆነ ቀጣይነት እንዲኖረው በተሳታፊዎች አስትያየት ተሰጦ ውይይቱ  ተጠናቋል።


ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ወጣቶች ክፍል

Thursday, October 23, 2014

ቀጣዩ የኢሕአዴግ ዒላማ ማኅበረ ቅዱሳን ይኾን?

ተመስገን ደሳለኝ  ስለማኅበረ ቅዱሳን ከአመት በፊት ....................... 
(ፋክት መጽሔት፤ ቅጽ 2 ቁጥር 14 መስከረም ፳፻፮ ዓ.ም. በተመስገን ደሳለኝ
የኢሕአዴግ ታጋዮች የመንግሥት ‹‹ጠንካራ ይዞታ›› የሚባሉ ከተሞችን ሳይቀር መቆጣጠር ችለዋል፤ ወደ አዲስ አበባም የሚያደርጉት ግሥጋሴም ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለ ማርያምን ሳይቀር ዕንቅልፍ ነስቷል፡፡ በአንዳች ተኣምር ግሥጋሴውን መግታት ካልቻሉ በጥቂት ወራት ውስጥ ሁሉም ነገር ታሪክ እንደሚኾን በማወቃቸው መላ በማፈላለጉ ላይ ተጠምደዋል፡፡ በዚህን ጊዜ ነበር(የሐሳቡ አመንጪ ተለይቶ ባይታወቅም)፣ ‹‹ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አጭር ሥልጠና ሰጥቶ ከሀገሪቱ ሠራዊት ጎን ማሰለፍና የ‹ወንበዴውን ጦር› መድረሻ ማሳጣት›› የሚለው ሐሳብ እንደ መፍትሔ የተወሰደው፡፡
እናም መንግሥቱ ራሳቸው ተማሪዎቹን በዩኒቨርስቲ አዳራሽ ሰብስበው እንዲህ ሲሉ አፋጠጧቸው፡- ‹‹እነርሱ (ኢሕአዴግና ሻዕቢያን ማለታቸው ነው) ለእኵይ ዓላማቸው ከእረኛ እስከ ምሁር ሲያሰልፉ እናንተ ምንድን ነው የምትሠሩት? በሰላማዊ ሰልፍና በስብሰባ ብቻ መቃወም ወይስ ወንበዴዎቹ እንዳደረጉት ከአብዮታዊ ሠራዊታችነ ጎን ቆማችኹ የአገሪቱን ህልውና ታስከብራላችኹ?››
ይህን ጊዜም አስቀድሞ በተሰጣቸው መመሪያ ከተማሪው ጋራ ተመሳስለው በአዳራሹ የተገኙት የደኅንነት ሠራተኞችና የኢሠፓ ካድሬዎች ‹‹ዘምተን ከጠላት ጋራ መፋለም እንፈልጋለን›› ብለው በስሜትና በወኔ እየተናገሩ በሠሩት ‹ድራማ› ተማሪው ትምህርት አቋርጦ እንዲዘምት ተወሰነ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም ተዘጋ፤ ተማሪዎቹም ለወታደራዊ ሥልጠና ደቡብ ኢትዮጵያ ወደሚገኘው የብላቴ አየር ወለድ ማሠልጠኛከተቱ፡፡
ከመላው ዘማቾች [የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ የኾኑ ሠልጣኞች በማሠልጠኛው ባዶ ድንኳን] በየጊዜው እየተሰበሰቡና በመጨረሻም ካምፓቸው አቅራቢያ ወደሚገኘው ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ከመዐቱ ይታደጋቸው ዘንድ ፈጣሪያቸውን በጸሎት መማጠን የሕይወታቸው አካል አደረጉት፤ ከቀናት በኋላም በአንዱ ዕለት አንድም ለመታሰቢያና ለበረከት. ሁለትም ስብስቡ ሳይበተን ወደፊት እንዲቀጥል በሚል ዕሳቤ‹‹ማኅበረ ሚካኤል›› ብለው የሠየሙትን የጽዋ ማኅበር መሠረቱ፡፡ . . . ይኹንና ከመካከላቸው አንዳቸውም እንኳ በ፲፱፻፸፯ ዓ.ም በፓዌ መተከል ዞን የተደረገውን የመልሶ ማቋቋም ሠፈራ ፕሮግራም እንዲያመቻቹ በዘመቱ ተማሪዎች ከተመሠረተውና ከተለያዩ የጽዋ ማኅበራት ጋራ በመዋሐድ የዛሬውን ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን›› እንደሚፈጥሩ መገመት የሚችሉበት የነቢይነት ጸጋ አልነበራቸውም፤ የኾነው ግን እንዲያ ነበር፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን
የ‹‹ማኅበረ ሚካኤል›› መሥራቾች ከተማሪ ጓደኞቻቸው ጋራ ‹‹ይለያል ዘንድሮ የወንበዴ ኑሮ››ን እየዘመሩ የገቡበት ወታደራዊ ሥልጠና ተጠናቅቆ ወደ ጦር ሜዳ ከመግባታቸው በፊት ዐማፅያኑ አሸንፈው የመንግሥት ለውጥ በመደረጉ ወደየመጡበት ተመለሱ፡፡ ኾኖም ለውጡ በተካሄደ በዓመቱ እነርሱን ጨምሮ በአምላካቸው፣ በጻድቃን፣ በሰማዕታትና በመላእክታት ስም የተመሠረቱ[ከአቡነ ጎርጎርዮስ ዘንድ ሲማሩ የቆዩ] የተለያዩ ማኅበራት ተሰባስበው ወደ አንድ እንዲመጡ መደረጉ ሊጠቀስ የሚገባ ልዩነት ባይፈጥርም ስያሜው ግን ብርቱ ክርክር አሥነሳ፤ አቡነ ገብርኤልም ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ብዬዋለኹ›› ብለው ውጥረቱን አረገቡት፡፡ ዕለቱም[ልደቱን የሚቆጥርበት] ግንቦት ፪ ቀን ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. እንደነበር ተጽፏል፡፡
ዓላማው ምንድን ነው?
ማኅበረ ቅዱሳን ሲመሠረት ዓላማዬ ብሎ የተነሣበት መሠረታዊ ጉዳይ በተለያየ ጊዜ ለኅትመት ባበቃቸው ድርሳናቱ ተገልጧል፡፡ እርሱም፡- [የቤተ ክርስቲያኒቱ] ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዐተ እምነት፣ ክርስቲያናዊ ትውፊትና ታሪክ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለ ማስቻል ነው፡፡
ማኅበሩ ከመሰሎቹ የተለየ ጥንካሬ እንዲኖረው ያስቻለው ዓላማውን ከግብ ለማድረስ በዋናነት በሀገሪቱ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆች የሚማሩ ተማሪዎችን አባል ማድረጉ ላይ ተግቶ መሥራቱ ነው፡፡ ዛሬም ድረስ መስፈርቱ እያገለገለ እንደኾነ ይታወቃል፤ ይህ ኹኔታም ይመስለኛል አንዳንድ ጸሐፍት ማኅበሩን ‹‹ቤተ ክርስቲያኗ በዩኒቨርስቲዎች ያላት እጅ›› እንዲሉት ያስገደዳቸው፡፡
የኾነው ኾኖ ማኅበሩ በምሥረታው ማግሥት በሃይማኖቱ የመጨረሻውን ሥልጣን በያዘው ቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅና ተሰጥቶት በጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር እንዲኾን ተደረገ፡፡ በ፲፱፻፹፭ ዓ.ም. ደግሞ መተዳደርያ ደንቡን አጸደቀ፡፡
የግጭት ጅማሬ
. . . አንዳንድ የኢሕአዴግ አመራሮች በብላቴ ከተመሠረተው ‹‹ማኅበረ ሚካኤል›› ጋራ በማያያዝ የማኅበሩን መሪዎች አልፎ አልፎ ‹‹ተረፈ ደርግ›› እና ‹‹መአሕድ›› እያሉ ከማሸማቀቅ ባለፈ ብዙም ጫና አያደርጉባቸውም ነበር፡፡ ዛሬ ማኅበሩን በመንግሥት ጥቁር መዝገብ በቁጥር አንድ ጠላትነት እንዲሰፍር ካደረጉት ልዩነቶች(ያለመግባባቶች) መካከል ዋናዎቹን በአዲስ መሥመር እጠቅሳለሁ፡፡
ኢሕአዴግ የአገሪቱን ምሥረታ ከዐፄ ምኒልክ ዘመን የሚጀምር የመቶ ዓመት ማድረጉ ማኅበሩ ዓላማዬ ከሚለው ‹‹ታሪክን ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ›› ጋራ መታረቅ አለመቻሉ ያስከተለው ውጥረት የመጀመሪያው ነው፡፡ ማኅበሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ታሪክ 2000 ዓመት ወደኋላ ሄዶ ማስላቱ ብቻውን፣ ‹‹አንዲት ኢትዮጵያን በመፍጠር ስም ምኒልክና ተከታዮቹ ያስፈኑትን ጭቆና በጠመንጃ ለማስወገድ በረሓ ገባን›› ከሚሉት የህወሓት መሥራቾች ጋራ ሊያጋጨው መቻሉ የሚጠበቅ ነበር፡፡ ጉዳዩን ከለጠጥነው ደግሞ ‹‹ማኅበሩን በ1980ዎቹ አጋማሽ እንደ ስጋት ይመለከተው የነበረውን ‹የሸዋ ፊውዳል› ወደ ሥልጣን ለማምጣት ያደፈጠ ተቃናቃኝ አድርጎ ፈርጆት ነበር›› ወደሚል ጠርዝ ሊገፋን ይችላል፡፡ በነገራችን ላይ፣ በፖሊቲካው መንገድ ለሹመት የበቁት አቡነ ጳውሎስም እስከ ኅልፈታቸው ድረስ ማኅበሩ በሸዋ ተወላጅ ጳጳስ ሊተካቸው የሚያሤር ይመስላቸው እንደነበር ይነገራል፡፡
በጥቅሉ በኢሕአዴግና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል የርእዮተ ዓለም (በብሔር እና በኢትዮጵያዊነት ላይ የተመሠረተ) ልዩነት መኖሩ ላለመግባባቱ መነሾ ነው፡፡
ሌላው የቅራኔአቸው መንሥኤ፣ በወርኃ ሚያዝያ ፲፱፻፺፫ ዓ.ም ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያምና ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጋራ ሰብአዊ መብትንና አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ባደረጉ ማግሥት፣ በዋናው ግቢ ከተቀሰቀሰው ተቃውሞ ጋራ የሚያያዘው ኹነት ነው፡፡ በወቅቱ ተማሪዎቹ በሰላማዊ መንገድ ላቀረቡት ጥያቄ የጸጥታ አስከባሪዎች የኃይል ምላሽ መስጠታቸው ጉዳዩን ከቁጥጥር ውጭ አደረገው፡፡ ድብደባውና ማሠቃየቱ ከአቅም በላይ የኾነባቸው የተወሰኑ ተማሪዎችም ከመንበረ ፓትርያርኩ በአጥር ወደሚለየው ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሸሽተው ይገባሉ፡፡ በአካባቢው የነበሩ የጸጥታ ሠራተኞችም የግቢውን በር ይቆልፋሉ፤ ተማሪዎቹንም በኃይል አስወጥተው ደብድበው አሰሯቸው፤ ድርጊቱንም ማኅበረ ቅዱሳን በስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ የቤተ ክርስቲያኗን ለሸሸ መጠለያነት ታሪክ አጣቅሶ አጠንክሮ መቃወሙ ከመንግሥት ጋራ በዐደባባይ ቅራኔ ውስጥ ከተተው፡፡
ሌላው ቅራኔአቸውን ያጦዘው ክሥተት ደግሞ በአቶ ተፈራ ዋልዋ በ፲፱፻፺፰ ዓ.ም ወርኃ ጥቅምት ‹‹መንግሥትና አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› በሚል ርእስ ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሥልጠና በተሰጠበት ወቅት ኦርቶዶክስን ‹‹የነፍጠኞች ምሽግ››፣ ጥምቀቱንም ‹‹በውኃ መንቦጫረቅ›› ብሎ ማጣጣሉ ሲኖዶሱን ግድ ባይሰጠውም፣ ማኅበረ ቅዱሳንን አስቆጥቶ መልስ እንዲሰጥ ያደረገበት ኩነት መፈጠሩ ነበር፡፡
የመዋቅሩ ስፋትና የውጥረቶቹ ጡዘት
የማይቆጣጠረውን የተደራጀ ኃይል አጥብቆ ለሚፈራው ኢሕአዴግ፣ የማኅበሩ መዋቅር እየሰፋ መሄድ ስጋት ላይ ጥሎታል፡፡ አባላቱ የዩኒቨርስቲ ወይም ኮሌጅ ምሩቃን መኾናቸው ከገጠር እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ድረስ የራሱ ሰዎች እንዲኖሩት አድርጓል፡፡ የአገዛዙም ጭንቀት ‹‹ይህ ኃይል አንድ ቀን በተቃውሞ ፖሊቲካ ሊጠለፍ ይችላል›› የሚል ነው፡፡ ይህንንም የሚያረጋግጠው አቶ ኣባይ ፀሃየ መስከረም ፲፪ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. የማኅበሩን አመራር በሲኖዶስ ጽ/ቤት ባነጋገረበት ወቅት ‹‹ኢሕአዴግ ገለልተኛ የሚባል ነገር አይገባውም›› የሚል መኾኑን ስናስታውስ ነው፡፡
. . .በኢሕአዴግና በቅንጅት መካከል በድኅረ ምርጫ – 97 የተፈጠረውን አለመግባባት ቤተ ክርስቲያኗ የቄሣርን ለቄሣር ብላ ለማንም ሳትወግን ዕርቅ እንዲፈጠር መሸምገል እንዳለባት ማኅበሩ በልሳኖቹ መወትወቱ የተገላቢጦሽ አገዛዙን አስኮረፈው፡፡ በአናቱም ከአማራ ክልል የተላከው ሪፖርት፣ ‹‹በገጠር ያሉ የማኅበሩ አባላት ለተቃዋሚዎች ቀስቅሰዋል›› ማለቱ ውጥረቱን አንሮታል፡፡
በሌላ በኩል መንግሥት ለሦስተኛ ጊዜ ባካሄደው የሕዝብ ቆጠራ ‹‹የ[ኦርቶዶክስ]ክርስቲያኑ ብዛት 33 ሚልዮን ነው›› ማለቱ፣ ‹‹[የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያን መረጃ በመጥቀስ] 45 ሚልዮን ነው›› ከሚለው ማኅበረ ቅዱሳን ጋራ አለመግባባት ውስጥ ከቶት እንደነበር ይታወሳል፡፡
የኢሕአዴግ ክሦች
ኢሕአዴግ በ፲፱፻፺፱ ዓ.ም በጅማ ከአጋሮ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው በሻሻ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ካህናትና ምእመናን ‹‹የእስልምና እምነት ተከታዮች ናቸው›› በተባሉ አንገታቸው በስለት ተቆርጦ መገደላቸውን የሚያሳየውን ፊልም በሲዲ አባዝቶ ያሰራጨውም ኾነ ከጭፍጨፋው ጀርባ የመንግሥት እጅ አለበት የሚል የስም ማጥፋት ዘመቻ የመራው ማኅበሩ ነው ብሎ ያምናል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በአዲስ አበባ ‹‹ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት››፣ በጎንደር ‹‹ጎዶልያስ›› (የእግዚአብሔር ጦር) የሚል ጽሑፍ የታተሙባቸው ቲሸርቶች አዘጋጅቶ ያሰራጨው ማኅበረ ቅዱሳን ነው ሲል ይከሳል፡፡ በነሐሴ ወር ፳፻፭ ዓ.ም በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም ስም ‹‹የአክራሪነት/ጽንፈኝነት ዝንባሌዎችና መፍትሔዎቻቸው›› በሚል ርእስ የተሰራጨው ሰነድ ክሡን፡- ‹‹ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ነች፤ አንድ አገር አንድ ሃይማኖት ወዘተ ጉዳዮችን በማቅረብ በአንድ በኩል የሃይማኖት ብዝኃነትን የሚፃረር፣ በሌላ በኩል ደግሞ አገራችን የሃይማኖት ብዝኃነት መኾኗን የሚቃወም አካሄድ ነው፤›› ሲል ያጠናክረዋል፡፡
የኦቦይ ስብሃት – ኩዴታ
በ፳፻፩ ዓ.ም ፓትርያርኩ አቡነ ጳውሎስ ከሲኖዶሱ ጠንካራ ተቃውሞ አጋጥሟቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡ ይኹንና ከዚህ ንቅናቄ ጀርባ አቡነ ሳሙኤልና ሁለት የማኅበረ ቅዱሳን አመራር አባላትን የያዙት ኦቦይ ስብሃት ነጋ እንደነበሩበት ለጉዳዩ ቅርብ ከነበሩ ሰዎች አረጋግጫለኹ፡፡ አቦይ ስብሃት ‹‹አቡነ ጳውሎስ ለኢሕአዴግ ዕዳ ነው›› ብለው መደምደማቸው ለኩዴታ እንዳነሣሣቸው ይነገራል፡፡
. . .[በተቃውሞው] ውጤት ፓትርያርኩ አሸነፉ፡፡ በወቅቱ ማኅበሩ የእንቅስቃሴው ተቃዋሚ መኾኑን የተረዱት አቦይ ስብሃት ነጋ ጥርስ እንደነከሱበት ይነገራል፡፡ በነገራችን ላይ፣ የአቦይ ዕቅድ ቢሳካ ኖሮ ተያይዘው የሚነሡ አለመግባባቶችን በመጠቀም ማኅበሩን መምታትንም የሚያካትት ነበር፡፡
የዋልድባ ጉዳይ
በመንግሥትና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል የነበረውን አለመግባባት ወደላቀ ጠርዝ ያደረሰው በዋልድባ ገዳም አካባቢ ይቋቋማል የተባለው የስኳር ፋብሪካ ጉዳይ ነው፡፡ በገዳሙ የሚኖሩ ምእመናንን ጨምሮ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች ያሰሙትን ተቃውሞ ችላ በማለት ወደ ሥራ ለመግባት በሞከረው መንግሥት ላይ የተነሣው ተቃውሞ ተጠናክሮ ቀጠለ፡፡ ይኹንና ሥርዐቱ ገዳሙ ላይ አልደርስም ብሎ ሲከራከር፣ ቤተ ክህነትም የማጣራት ሥራ መሥራቱን ገልጦ ‹‹ምንም ዐይነት ችግር የለም›› ብሎ ከመንግሥት ጎን ቆመ፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ጉዳዩን ቦታው ድረስ ሄዶ የሚያጣራ አምስት አባላት ያለው ቡድን ወደ ዋልድባ ላከ፡፡ ቡድኑ አጥንቶ ባቀረበው ሪፖርት፡- ‹‹16.6 ሄክታር መሬት ከገዳሙ ተወስዷል፤ ገዳሙን የውኃ መጥለቅለቅ ያሰጋዋል፤ . . .›› የሚል ሪፖርት ለመንግሥት አቅርቧል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ የዶ/ር ሽፈራው ሰነድ የማኅበሩን ጥናት እንዲህ ሲል ኮንኖታል፡- ‹‹መንግሥት በሃይማኖታችን ጣልቃ ገብቷል በሚል ገሃድ ፍላጎትና ድብቅ አሠራር ካላቸው የውጭ ቡድኖች ጋራ በማበር ሰላምን አደጋ ውስጥ የማስገባት፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱን በሃይማኖት ሽፋን ለመናድ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ በቅርብ በነበረው የፓትርያርክ ምርጫና በዋልድባ ገዳም ዙሪያ የተፈጠረው ዝንባሌ የነዚህ ፍላጎቶች ማሳያ ነው፡፡››
የፓትርያርኩ ኅልፈት
በ፳፻፬ ዓ.ም መጨረሻ አቡነ ጳውሎስ ማለፋቸው ሌላ ፍጥጫን አስከትሏል፡፡ ማኅበሩ ስደተኛውን ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስን ከአሜሪካ አምጥቶ ወይም እንዳሻው የሚያሽከረክረውን ጳጳስ መንበሩ ላይ ለማስቀመጥ ምርጫው በሚፈልገው መንገድ እንዲጠናቀቅ በርትቶ እየሠራ ነው የሚለው ወቀሳ የመንግሥት ቁጣን የበዛ አድርጎታል፡፡ የጠቀሱት ሰነድም ውንጀላውን በገደምዳሜ ገልጾታል፡- ‹‹በእስልምናም ይኹን በክርስትና ሃይማኖቶች ሽፋን የሚደረገው የአክራሪነት/ጽንፈኝነት እንቅስቃሴ በዋናነት እያነጣጠረ የሚገኘው የተቋማቱን የበላይ አመራር ዕርከኖች መቆጣጠር ነው፡፡››
ናዳው እየመጣ ነው?
ባለፉት ሁለት ዓመታት የእስልምና እምነት ተከታዮች ‹‹መንግሥት በሃይማኖታችን ጣልቃ አይግባ›› በሚል የጀመሩትን ትግል ተከትሎ አገዛዙ ማኅበረ ቅዱሳንንም ደርቦ የመምታት ዕቅድ እንዳለው የሚጠቁሙ ምልክቶች ታይተዋል፡፡ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤትን በሚኒስትር ማዕርግ የሚመራው አቶ ሬድዋን ሑሴን፣ ‹‹መንግሥት ጉዳዩን በሰላም ቢጨርሰው የተሻለ ነው›› ሲሉ ምክር ለመለገሥ ለሞከሩ የምዕራብ አገሮች ዲፕሎማቶች፣ ‹‹የአወሊያን ቡድን በዚህ መልኩ ሳናበረክከው ቀርተን መጅሊሱን እንዲወስድ ብናደርግ፣ ነገ ደግሞ ማኅበረ ቅዱሳን ‹ሲኖዶሱን አምጡ› ቢለን ምን መለስ ይኖረናል?›› ሲል የሰጠው ምላሽ ይህንኑ የሚመለክት ነው፡፡
የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር መ/ቤት ባለፈው ዓመት ወርኃ የካቲት ‹‹ለሃይማኖት ተቋማት የተዘጋጀ›› ብሎ ያሰራጨው ሰነድ ማኅበረ ቅዱሳንና መብታቸው እየጠየቁ ያሉ የእስልምና እምነት ተከታየች የጥቃቱ ዒላማ እንደኾኑ ያሳያል፡፡ ሂደቱን በመምራትም ኾነ በማስፈጸም ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ጀርባ ኾኖ በዋናነት የሚሠራው የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል እንደኾነ ይታወቃል፡፡ ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም ‹‹የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፖሊቲካ ርብርብ ሜዳ አይኾኑም፤ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችም ከማንኛውም ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ ነጻ መኾን አለባቸው›› ያሉበት ዐውድ ‹‹በዩኒቨርስቲዎች የአካዳሚ ትምህርትን ተገን በማድረግ እምነትን ማስፋፋት አይቻልም›› በማለት ማኅበሩ እንደ ቀድሞው አባላቱን ለመሰብሰብና ለማስተማር የሚችልበትን ኹኔታ የሚያግድ ነው፡፡
በ፳፻፮ ዓ.ም በዩኒቨርስቲዎች ይተገበራል የሚባለው አለባበስንና አመጋገብን የሚመለከተው መመሪያም ራሱን የቻለ አደጋ አለው፡፡ እንዲሁም የሃይማኖት ማኅበራት ዓላማቸውን አሳውቀው እንዲመዘገቡ የሚያስገድደውን ሕግ በምክር ቤት ለማጸደቅ ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡ መዝጋቢው ክፍል ማኅበራቱን በፍርድ ቤት ከማስቀጣት እስከ ማፍረስ የሚያደርስ ሥልጣን እንደሚሰጠው ምንጮቼ መረጃ አድርሰውኛል፡፡ ይበልጥ የንደነግጠው ደግሞ በዚህ መልክ ማኅበራቱን ከጠለፉ በኋላ ማንም ሰው ‹‹ቅዱስ ቃሉን›› ለመስበክ ፈቃድ ማግኘትን ግዴታ ለማድረግ መታቀዱን ስናነብ ነው፡-
‹‹የሰባክያን/ዳኢዎች ሚናን የበለጠ ለማጎልበትና የተጠያቂነት ሥርዐት ለመትከል እያንዳንዱ የሃይማኖት ተቋም የራሱን መምህራን የሚለይበትን የመታወቂያ ሥርዐት ሊያበጅና በዚህም የክትትል ሥራ እንዲሠሩ መደገፍ ይቻላል፡፡››
ሰነዱ ወደ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሚገቡ ተማሪዎችንም መልምሎ የሲኖዶሱን፣ የማኅበረ ቅዱሳንን፣ የመጅሊስን. . .አመራርነት የመያዝ ዕቅድ እንዳለው በዘወርዋራ ይጠቁማል፡፡ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በ፳፻፬ ዓ.ም ባዘጋጀው የሥልጠና ማንዋል ላይም ‹‹በኦርቶዶክስ ክርስትና መድረክ አክራሪው ኃይል ማኅበረ ቅዱሳን ነው›› ሲል መፈረጁ ይታወሳል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎንም የማኅበረ ቅዱሳንን ግቢ ጉባኤ በማዳከም፣ ከሰንበት ት/ቤቶች፣ ከሰበካ ጉባኤና ከሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች ጋራ በማጋጨት፣ በካህናት በማስወገዝና በመሳሰሉት ተጠቅሞ ሊያፈርሰው እንደተዘጋጀ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በጥቅሉ ሰነዱ ማኅበረ ቅዱሳንን ‹‹በሃይማኖት ሽፋን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት መንግሥታዊ ሃይማኖት መኾን ይገባዋል በሚል በአቋራጭ የፖለቲካ መሣርያ ለማድረግ የሚንቀሳቀስ›› ሲል ይኮንነዋል፡፡ ‹‹የአክራሪነትና ጽንፈኝነት ምንጩን ለማድረቅ እየተሠራ የሕግ የበላይነትን የማስከበር ሥራም ጎን ለጎን መፈጸም ያለበት ነው፤›› ሲል ጥቁምታ ይሰጣል፡፡
መፍትሔው ምንድን ነው?
ከላይ በጥቅሉ እንደጠቀስኩት የ22 ዓመታቱ ሂደት የሚያስረግጠው፣ የኢሕአዴግን ማንኛውም ዓለማዊም ኾነ ሃይማኖታዊ ተቋማት ነጻነት ያለማክበሩ ብቻም ሳይኾን ቀስ በቀስ ህልውናቸውን ለዘላለሙ ለማጥፋት በሙሉ ኃይሉ እየሠራ እንደኾነ ነው፡፡
የኾነው ኾኖ የማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች ተቋማቸውን ለመከላከል . . .ሕዝበ ክርስቲያኑ ሕዝባዊ ንቅናቄ ፈጥሮ በመከራው ጊዜ የደረሰለትን ‹‹የእምነቱን ዘብ እንዲታደግ›› ጥሪ ማስተላለፍና ማነሣሣት ይጠበቅባቸዋል፡፡
. . . ማኅበሩ ዝምታውን በመግራት የራሱን ህልውና እጅግ በፍጥነት ለመታደግ መሞከር ይኖርበታል፡፡ ከሥርዐቱ የፖሊቲካ ዘዬ እንደተረዳነው፣ ቀስ በቀስ እየጠበቀ በመጣው አፈና ላይ ማኅበሩ አንገቱን ቀብሮ፣ ጣልቃ ገብነቱን ቸል ብሎ የማንገራገሩ አካሄድ፣ በአንድ ክፉ ቀን በመጅሊሱ የተፈጸመው ታሪክ በራሱም ላይ መደገሙ አይቀሬ እንደኾነ ለመናገር ነቢይ መኾንን አይጠይቅም፡፡ የትምህርት ተቋማትን የረገጡ ከተሜ ወጣቶች በማኅበሩ ውስጥ መብዛታቸው የመውጫ መንገዱን በአመራሩ ላይ ይጥለዋል፤ ‹‹ለትላንት አናረፍድም፤ ለነገ አንዘገይም›› እንዲሉ የቤተ ክርስቲያኗ ሊቃውንት፡፡

Monday, October 20, 2014

Is Nonviolent or armed struggle for bringing democracy in Ethiopian?


As we know, Ethiopia is a home to golden diversity of peoples, cultures, religions and languages. Ethiopia is as the origin of humanity that has a unique cultural heritage, own alphabet, calendar and where it has preserved its long independence through the patriotic struggle of its citizens. We shall remember that Ethiopia served as a symbol of African independence throughout the colonial period, and was a founder member of the United Nations and the African base for many international organizations and country that possesses a long history ranking among the great civilizations of the world.
But currently, it has not been possible to have human and democratic rights guaranteed by the Constitution fully respected. The question of nations and nationalities is not properly addressed and resolved. In fact, the issue is presently being used as a tool for dividing and ruling the people. Citizens are being deprived of the opportunity to live, work and to do any kind of activities in the country whether socially, economically and politically. The integration process among the nation, nationalities and peoples are being disrupted. Now a day’s, Ethiopia is among the most backward countries in the world in three aspects which is political, economical and social growth because of these, It’s known that TPLF is a dictatorship ruling party and has never showed let down peacefully, and Woyane is doing shameful activities throughout the country since they took power through armed struggle. Woyane is doing shameful activities throughout the country since they took power. Such as, many journalists, politicians, activists, bloggers, religious have been imprison, thousands of peoples are dying and many people’s migrating every day, no single human right respected by TPLF. As the nature of TPLF I have doubt that nonviolent struggle would be successful in Ethiopia. I never shared the illusion that the TPLF will accept the verdict of the ballot-box and step down from power peacefully rather the TPLF play the democratic game under the name of democracy. Murdering, genocide, criminal, dictatorship, corrupting, selfishness, future less, narrow thinking and no need solid unitary as a country (means follow dividing ruling system) are the main Characteristics of TPLF.
Due to the nature of TPLF, I just to reflect a few points of view on the question of peaceful or armed struggle as methods of achieving a political goal like to bring freedom, justice and democracy in Ethiopia. In other words, the very challenging question is whether to apply peaceful or armed; or the combination of the two based on a given internal political reality, and external circumstance to bring sustainable democracy. Needless to say, this had been and continues to be an unavoidable challenge in a country like ours which has never experienced a political transformation characterized by a well- thought, well-planned, well-organized and persistent popular uprising and disobedience in line with the fulfillment of the interests of the general public.
I sincerely believe that we should be seriously concerned about our tendency of approaching the question of which method of political struggle should we apply in a very categorically defined fashion. Although raising the question of how to approach a given political struggle that aims at the realization of a democratic political system has never been uncommon, its intensity and urgency varies from time to time, and from situation to situation. Because of our political culture which is characterized by mere inheritance, conspiracy within royal families and a bloody fight between or among groups (civil war), we are not yet fortunate enough to listen to each other’s arguments and counter- arguments in such a way that our differences on using not the same tactics or methods should not hamper our journey toward the same goal.
I strongly believe that it is absolutely necessary to seriously consider the advantages and disadvantages of a given method of getting the goals and strategies we set accomplished in a real sense of constructive way of doing things accordingly the Ethiopian political situation. In other words, it is imperative to make sure that the methods being used by various political groupings (surprisingly there are more than 90 national and regional political parties) which are engaged in the struggle for the realization of a truly democratic society complement each other in pursuing for mutually respectful and shared prosperity. Is this line of thinking as easy as anything? Absolutely not! And this is mainly because of our political history and which has been and still is characterized either by very deceptive monarchial rulers or get it at a bloody gunpoint like TPLF. And this very unfortunate political culture of ours has a lot of to do with the argument that it is nonviolent/peaceful resistance not armed struggle that is ideal to bring about sustainable democratic change. Yes, there is no doubt peaceful public struggle is so desirable. The very challenging issue is when it comes to the question of what kind of ruling power we face – with a sense of civility and responsibility or otherwise? How the people are ready and determined to pay the sacrifices required forcing the brutal responses by the ruling elite even in the process of peaceful struggle; how various opposition political forces are willing and able to pull their efforts together and shake the balance of the existing political power? Are the foreign powers (governments) interested and courageous enough to abandon “their bad guys “and choosing people’s interests over dictatorial regimes? To my understanding, the responses to these and all other critical questions are not encouraging at all.
Unless we want to remain wishfully optimistic, it is very unwise to waste our energy and time by continuing arguments and counter arguments to the extent of condemning each other’s tactics applied to get the same goal done. I am not saying debating or arguing on the prospective and consecutive of peaceful resistance and armed struggle or on how to effectively use both of them is a bad idea. What I am trying to say is that it is critically desirable to focus on how to make those methods of struggle vibrant forces toward achieving the same goal – the realization of genuine democratic society and fundamental human dignity. I understand that opposition political parties which are operating legally and pursuing peaceful resistance cannot openly recognize the use of armed struggle. I know very well that doing so is suicidal as far as the very behavior and practice of the illegitimate ruling circle is concerned. Yes, in a truly democratic system expressing one’s idea freely is a not only a political freedom but it is also fundamental human freedom. Sadly enough, it is a crime (terrorism) in our country, and we are witnessing the untold sufferings of innocent journalists and members /supporters of political opposition parties. But, I strongly believe that although it is suicidal for those political parties to openly recognize those political forces which believe in the use of both methods of struggle ,they should not undermine ,if not condemn each other .
Indeed, I have fully agreed with the nonviolent struggle because of the merits of it. Whatever it is your argument, Ethiopia is required a systematic and friutfull struggle to bring freedom, justice, democracy and all human rights respected. What is needed is political work to influence the army and bureaucracy to make them less obedient instruments of repression, or to become sympathizers of civil disobedience.
The peaceful struggle may be painfully slow for the impatient. Yet, it is may or may not the only choice which truly induces the utilization of untapped artistic, cultural and intellectual wealth of the nation for the material and political maturity of citizens, essential elements for a successful establishment of a dynamic and democratic social order.

Nonviolent action used to:
• Dismantle dictatorships
• Defend against foreign invasions
• Expel foreign occupation
• Provide an alternative to violence in extreme ethnic conflicts
• Challenge unjust social and economic systems
• Develop, preserve and extend democratic practices, human rights, civil liberties and freedom of religion
• Resist genocide since carefully applied the methods of nonviolent action or “nonviolent weapons.” The Albert Instinet institution has recommended almost nearly two hundred methods of nonviolent struggle. (See on aeinstein.org, list of 198 methods of nonviolent action and also The Politics of Nonviolent Action, Vol. 2)

Three broad classes of nonviolent methods are:
1. Nonviolent protest and persuasion, like formal statements, wider audience, symbolic public acts,
2. Noncooperation and, (social, economic boycotts & strike, political)
3. Nonviolent intervention, (physiological, physical, social, economic and political intervention)

Like others, Ethiopia has tried to bring freedom, justice, democracy and human rights respected by nonviolent struggle in different time but could not successful due to our politics nature as I mentioned above. For example, different kinds of revolution, during 2005 election, the movement of Muslims, many opposition parties doing that still now.
Finally, I recommend that calling and wake upping the peoples, farmers, workers, business men, students, teachers, polices and defense force to struggle for themselves that freedom and justice, education and health, academic and political freedom, pursuit of prosperity and other rights are our rights that we are entitled to as citizens. They are by no means any acts of generosity given to us by the rulers who have imposed their will on us. These are rights that we should never relinquish to anyone. And I encourage values such as civil dialogue, tolerance, understanding and respect for competing views not only to narrow differences but also to nurture and sustain the unity of shared purpose to bring freedom and democracy in Ethiopia by choosing the most convenient struggle methods.

Wednesday, October 15, 2014

Obang Metho’s Timely Letter to the TPLF

Ato Obang Metho, the Executive Director for the Solidarity Movement for a New Ethiopia (SMNE) and the well-known human rights advocate among Ethiopians and friends of Ethiopia, recently sent a historic and principled letter to the leaders of the TPLF (www.solidaritymovement.org/amharic/140904-Open- the Amharic Letter-to-the-TPLF.pdf), highlighting the dangerous trajectory our country finds itself under the TPLF’s apartheid-like governance policy. It is a historic letter because no one has systematically documented a protest letter addressed to the leaders of the TPLF on the fundamentally flowed nature of their ethnic policy, the danger it poses for the future of our people, and the need to come-up with an all-encompassing alternative strategy. It is principled because the letter stems from a passion for fundamental freedom, human rights, and democracy for all Ethiopians and harbors no ill will or hatred toward anyone, including the TPLF leadership. In short, the letter is a clarion call for those responsible and their supporters to stop the ominous tumbling cascade and open-up to reform and reconciliation before things are out of hand and too late. It captures the agony of the present and the aspirations for the future. I see it as a challenge not only to the TPLF leadership and its members but to each one of us, regardless of our unique background, to take a critical look at the apartheid-like system foisted upon us and to adapt a principled position to seek a negotiated acceptable solution.
Ato Obang’s letter is respectful but does not mince words at pointing the dangers of ethnic politics and the incalculable damages it has already inflicted on Ethiopia and its people, including what it has done to Obang’s own ethnic group – the suspected murder of over 420 innocent ethnic Anuakes under the TPLF in 2003. Despite these atrocities, he holds no grudges and displays remarkable love and forgiveness toward his political opponents for the sake of lasting peace. His letter argues that ethnic politics is an abomination that is devoid of morality, ethics, religion, logic or the rule of law, hence must be discarded. Most importantly, it argues that such a system is nihilistic and antithetical to peaceful co-existence and the pursuit of sustainable development in a multi-ethnic, multi-religious country like ours. Ato Obang urges the TPLF leaders and their supporters to overcome their suspicion and fear and embrace Ethiopia and all Ethiopians.
The Ethnic federation of the sort the TPLF is dogmatically pursuing is not a benign, misguided policy but a toxic prescription that is eating away the social, cultural, and historic fabric that holds the people and the country together. What is scary is that it inhibits the cultivation of a common heritage, assimilation, and destiny essential for the healthy survival and growth of the nation. It has created an unhealthy “them” and “us” mentality among Ethiopians of all hues and persuasions, laying a fertile ground for pitting citizens against each other at the slightest sign of misunderstanding or discord. The pitfalls of such a misguided policy are in the open for any rational and sane person to see. As the direct result of officially-sanctioned policies of the TPLF and by virtue of its total dominance of the Ethiopian government, discrimination is openly exercised in budget and resources allocation among the regions and in the provision of government services. Citizens face blatant discrimination in employment, business, and educational opportunities. The country’s key economic sectors from banking and finance to industry, from transportation to communications, from health services to pharmaceuticals, and from agriculture to food processing have been systematically misappropriated by the TPLF and turned into lucrative financial spigots for the party and its supporters. The country’s key public institutions from defense to foreign affairs, from intelligence to immigration, from law enforcement to the security forces have been brought under the total control of the TPLF. They are disproportionately staffed by TPLF party hacks and loyalists and turned into party instruments for the suppression of dissent. As such, there is no clear demarcation between the TPLF and the government. Governmental institutions have been stripped off their independence and the rule of law has been crippled, and therefore, there is no avenue for redress. Essentially, the government is there to serve and advance not the interests of the people but that of the TPLF. We should not be fooled by Ethiopia’s much talked about economic progress, because any current achievement in the sector should not be confused with a broad-based sustainable economic progress that has taken root for the benefit of the majority.   
The independent media is obliterated, opposition politics is suppressed, civil society is stifled, and academic freedom is curtailed. The state media is co-opted into an instrument of propaganda to foster division, misinform and confuse, instill fear, and dehumanize critical voices. Religious and cultural institutions have been infiltrated and shamefully silenced from preaching the truth, justice, equality and freedom. As such, the TPLF has purposely closed off all possible avenues for constructive criticism, and in the proverbial sense, is dancing naked to its own discordant tune. In this type of stifling environment, brave gadflies emerge to tell the truth head-on and seek solutions. Ato Obang has become that sorely needed gadfly by courageously and publicly broaching the subject on everybody’s mind. His argument is that the blatant discriminatory policy of favoring TPLF members, who are exclusively from Tigray, over other citizens, is morally reprehensible, illegal, and should be rejected by all of us. That the party’s discriminatory policy is building resentment against the party and its political base and can no longer be ignored. That unless this injustice is remedied and the abhorrent policy reversed through dialogue and compromise, the accumulating grievance could nudge the nation into an ethnic conflict and undesirable outcomes. He sees it as our national duty to discuss the “elephant in the room” openly and candidly and seek a better model that would guarantee our common future and aspirations. In that sense, the letter carries our collective demand to end the subjugation of the multitude by the few and our yearning for a fair and equitable system.    
Thanks to Ato Obang, no self-respecting person can hide any longer behind shenanigans and illogical arguments to prop-up or ignore this morally-bankrupt and illegal system. Despite past disappointments, I for one, hope the letter would not fall on deaf ears. I am optimistic because it also directly appeals to our Tigrayan brothers and sisters to serve as bridges for the change we so desperately and urgently need. One thinks of Ato Abreha Desta, a compatriot who is paying dear price in TPLF dungeons for encouraging dialogue and reform. A brighter Ethiopia lays in the uplifting visions and sacrifices of Obang, Abreha, and multitude of others. I hope and pray that many other Tigrayans quietly agonizing behind the scene would come out in the open and encourage needed reconciliation and reform. I am sure such compatriots would find principled, reliable and solid partners in Ato Obang and like-minded reformers from all corners of Ethiopia.    
By the same token, it is disappointing, but not surprising, that some zealot TPLF hardliners and supporters have resorted to raw bigotry and foul language to attack Ato Obang for sending the historic and principled letter to their party and leaders. This attack is not just on Ato Obang but on each one of us. The TPLF and its supporters at minimum should apologize to Ato Obang, condemn the bigotry targeted at him in no uncertain terms, and take concrete action to expel such bigots from their party. Similarly, member and affiliate parties of the EPRDF should condemn this vile bigotry in the strongest terms possible and demand action from the TPLF, if they are indeed about equality and fairness and have a scintilla of independence. 
THANK YOU, Ato Obang for being the voice of the voiceless and an inspiration to millions!!!

Thursday, October 2, 2014

አቶ ሰለሞን ገ/ስላሴ ከአሜሪካ ተባረሩ

የኢትዮጵያ ኢምባሲ ባልደረባ የሆኑት አቶ ሰለሞን ገ/ስላሴ በ 48  ከአሜሪካ እንዲወጡ ታዘዙ:: ከአሜሪካ እንደወጡም የዜና ምንጮች ገለጹ።

የኢትዮጵያ ኢምባሲ ባልደረባ የሆኑት አቶ ሰለሞን ገ/ስላሴ በ 48 ሰአት ውስጥ ከአሜሪካ እንዲወጡ ታዘዙ:: ከአሜሪካ ተባረሩ አሁን በደረሰን ዜና መሰረት
ሰኞ ረፋዱ ላይ ኢትዮጵያኖች በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞአቸውን በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ላይ ተገኝተው ድምጻቸውን በማሰማት ላይ እንዳሉ የኢምባሲው ባልደረባና የአቶ ግርማ ብሩ ዘበኛ የሆኑት በኢትዮጵያኖች ላይ ጥይት ከተኮሱ በኋላ በደህንነት አባላት ታስረው በዲፕሎማት መብት ቢለቀቁም በ48 ሰአት ውስጥ ከአሜሪካን ሀገር እንዲወጡ የአሜሪካን መንግስት ማዘዙን ምንጮች አስታውቀዋል። አቶ ሰለሞን ከአሜሪካ መባረረራቸውን ምንጮች በድጋሜ አረጋግጠዋል።

በእለቱ ምንም አይንት ጉዳት ባይደርስም የአሜሪካን የጸጥታ ሃይሎች ጉዳዩን እየመረመሩት መሆኑን ቃላአቃባዮ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ አረጋግጠዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከኢትዮጵያ ኢምባሲ ጋዜጠኛ ነው ተብሎ በስቴት ዲፓርትመንት የጋዜጠኞች መግለጫ ላይ የተላከው የህወሃቱ ዘጋቢ በእለቱ ጥያቄ አለኝ በማለት የአሜሪካን ፕሬዝዳንት በትክክል መናገር አለመቻሉ የአለም ጋዜጠኞችን እና የስቴት ዲፓርትመንትን ከማሳቁም ባለፈ በዲሞክራሲያዊት አሜሪካ የሚደረገውን ሰላማዊ ተቃውሞ በጋዜጠኞች ፊት መተቸቱ የህዋትን ኢሰባዊና ኢዲሞክራሲያዊ ድርጊትን ይበልጥ አጋልጧል። በቦታው የተገኙትን ጋዜጠኞችም የኢትዮጵያን መንግስት ጋዜጠኞች የመንግሥት ተላላኪዎች ብቻ እንጂ ብቃት የለሌላቸው መሆኑን ለመረዳት ተችሎል።

በዚህ ከተቀጠለ ኢትዮጵያ አገራችን የነጻነትን ብርሃን ለማየት እድል ሊያጋጥማት እንደሚችል ብዙዎች ይናገራሉ።