Friday, June 19, 2015

ሰማዕትነት፦ ለዓላማ ሲሉ ማንኛውንም ዋጋ መክፈል መቻል ነው!

ሰማዕትነት ለሰው ልጅ እንግዳ  ነገር አይደለም። የነበረ፣ ያለና የሚኖር ነው። የሰማዕታት ተግባራትና ዓላማቸው የከበረ፣ ስማቸውም ዘላለማዊ በመሆኑ ትውልድና ታሪክ ሲያወሳቸው ይኖራል።
የሰማዕታትን ራዕይ፣ ዓላማና ተልእኮ ፍሬ እንዲያፈራ ማድረግ የትውልድ ታላቅ አደራ ነው።
አደራ መወጣት ከባድ ቢሆንም፤ የሀገር፣ ነጻነት፣ፍትህና ማንነት ብለው ሰማዕትነትን የተቀበሉ ሰማዕታት የሰጡንን አደራ በተገቢው መንገድ ከግብ እናደርሳለን። ራዕያቸውን ሰንቀን ወደፊት ከመጓዝ በቀር ከወያኔ ጋር በምንም በምን አንደራደርም።
ሰሞኑን በአሰቃቂ ሁኔታ በወያኔ አሸባሪ ቡድን በግፍ የተገደለው የህግ ባለሙያ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር፣ የፓርላማ እጩ ተወዳዳሪ፣ የነጻነት ታጋይ፣ ለሀገርና ህዝብ የቆመው ወጣት ሳሙኤል አወቀን እና የአረና ፓርቲ የፓርላማ እጩ ተወዳዳሪ ታደሰ አብርሃን በተመለከተ ዓለም አቀፍ ብዙኃን መገኛዎች በዜናቸው እንዲህ ለታሪክ ዘግበውታል።  

“ከታሰርሁም ህሊናዬ አይታሰርም ከገደሉኝም ትግሌን አደራ በተለይ የኔ ትውልድ አደራ! ተገደልሁም ታሰርሁም ነፃነት አይቀርም!” ሳሙኤል አወቀ

“ማንኛውም የምከፍለው ዋጋ ለሀገሬና ለነጻነት ነው፤ በአካል ብታሰርም ህሌናዬ አይታሰርም፣ ከገደሉኝም ትግሌን አደራ”   ~ በግፍ የተገደለው ሳሙኤል አወቀ

እኛም እንላለን፡፡ አደራህ ከባድ ነው፡፡ ቃልህን እናከብራለን፡፡ አላማህንም እናሳካለን!!!! (ሰማያዊ ፓርቲ)








ሳሚ፦  “ብታሰርም፣ ማንኛውንም ዋጋ ብከፍልም፣ ብገደልም ይህን ሁሉ የማደርገው ለሀገሬና ለነፃነቴ ነው” ያልከው ቃል /ህያው ሆኖ ለዘላለም በክብር በወርቅ ቀልም በልቦቻችን ተጽፎ ከመቃብር በላይ ይኖራል!!!! የሞትክለትን ዓላማ እናሳካለን፤ የአደራ ቃልህን እናከብራለን!!! መሪ ቢታሰርም ቢሞትም ትግል ግን ይቀጥላል . . .እንዲያውም ሚሊዮኖችን የነጻነት ታጋይ ተክቶ ያልፋ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
 ታዴ፦ የሞትክለት የነጻነት ትግል በዓላማህ ጽናት ታድሶ ትውልድ ተረክቦታል! የወያኔ ማፍያ ወሮበላ ቡድን የትግራይን ህዝብ ሊወክል እንደማይችል በግልጽ ለኢትዮጵያ ህዝብ አሳይተሃል!

ክብር ለሰማዕታት! ነጻነትና ፍትህ ለኢትዮጵያ ህዝብ! ውድቀት ለወያኔ ወሮበላ ቡድን ይሁን!!!


No comments:

Post a Comment