Tuesday, February 17, 2015

የአንዳርጋቸው ልደት በኖርዌይ

በዲሞክራሲያው ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የወጣቶች ክፍል አዘጋጅነት የአርበኛውና ጀግናው አንዳርጋቸው ጽጌ 60ኛ ዓመት የልደት በዓል ፌብሯሪ 14/2015 በተለያዩ ሰፊ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል። በኖርዌይ የሚገኙ ውድ ኢትዮጵያውያን በብዛት በበዓሉ ታድመዋል። የኢሳት ጋዜጠኛ ገሊላ መኮነንም ተሳታፊ ነበረች።
ያ ቀን ለእኔ ልዩ ስሜት እንዲሰማኝ አድርጎኛል። ሁለት ዓይነት ስሜት፡ አንደኛው አንዳርጋቸው ምንም እንኳ በዚች ልዩ ቀን በመካከላችን ባይገኝም የህይወት መስዋትነት የከፈለበትን የኢትዮጵያን የወደፊት ተስፋ ማለትም የነጻነት፣ የፍትህና የዲሞክራሲ በአጠቃላይ የዜጎቿ መብት የሚከበርበት ቀን እየቀረበ መሆኑን ሳስብ የደስታ ስሜት፤ በለሌላ በኩል ደግሞ አንዲ ለነጻነት ብሎ በአረመኔው ወያኔ የሚደርስበትን መከራና ስቃይ ሳስብ ደግሞ ሃዘን ተሰምቶኛል። 

The 60th Birhday celebration of Andy's Tsige in Oslo, Norway

በልደት በዓሉ ላይ የተለያዩ ዝግጅቶች ተከናውነዋል። ከነዚህም መካከል በዋናነት፦
· አንዳርጋቸው ማነው በሚል ሰፋ ባለ መልኩ ስለ አንዲ የህይወት ታሪክ፣ አላማ፣ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ውስጥ ያደረገው አስትዋጾ እና የወደፊት ራዕይ ለታዳሚው በሚገባ ገለጻ ተሰጧል
· በመቀጠልም የአንዳርጋቸውን ታሪክ የሚዳስስ አጭር ፊልም ቀርቧል፣
· በቅርበት ከሚያውቋቸውና ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ውህደት ወደ አስመራ በሄዱት በዶ/ር ሙሉአለም አዳም ስለ አንዳርጋቸው ማንነት እንዲሁም አንዳርጋቸው በወያኔ እጅ ከተያዘ በኋላም ህዝባዊ ኃይሉ ይበልጥ እየተጣነከረ መምጣቱን የአይን ምስክርነት ሰጠዋል፣
· በእየፕሮግራሙ መካከልም አቶ አንዳርጋቸውን የሚያወድሱና ስለጀግንነቱ የሚያወሩ የተለያዩ መጣጥፎች ቀርበዋል፣ ለምሳሌ አንዳርጋቸው፣ ሰው የሚወለደው፣ የአንዳርጋቸው ልደት፣ ለአንቺ ነው ኢትዮጵያና ፈርተህ አታስፈራኝ በሚሉ ርዕሶች ግጥም ቀርቧል።

                         ግጥም በኤልሳቤጥ ግርማ 
በአቶ ማተቤ መለሰ
· በበዓሉ ላይ የተገኙ ኢትዮጵያውያን ለአንዲ ያላቸውን አክብሮት ይገልጹ ዘንድ የሃሳብ መስጫ ጊዜ ነበር። በዚህም ብዙዎች አንዳርጋቸውን እንሁን፣ እርሱን እንላበስ፣ የእርሱን መንገድ እንከተል፣ ፍርሃትን፣ አድር ባይነትን እናሶግድ፣ አንዲ የሰጠንን ታላቅ አገራዊ ተልእኮ እንፈጽም፣ ራዕዩን ከግብ ለማድረስ ቆርጠን እንነሳ፣ ቃል እንግባ በማለት ሃሳባቸውን ገልጸዋል።
በመጨረሻም ለልደት በዓሉ የተዘጋጀው ሻማ ተለኮሰ። አንዲ የለኮሰውን የነጻነት ብርሃን ምሳሌ ይሆን ዘንድ ሻማው እንዲበራ ተደረገ። አንዲ እራሱ አቅልጦ እኛን ነጻ እንዳደረገ ምሳሌ ትሆነው ዘንድ ሻማው እየቀለጠ ብርሃን እንዲፈነጥቅ ተለኮሰ። ለክብሩ የተዘጋጀው ኬክ በስሙ ተቆረሰ አንዲ በአካል ባይኖርም በመንፈስ ከእኛ ጋር ሁኖ ኬኩን እንዲቆርስ እንጋብዘዋለን! አንዲ የማይጨበጥ፣ የማይዳሰስ መንፈስ ነውና።
ሁላችንም “እኔ አንዳርጋቸው ነኝ” በማለት ቃል በመግባት በአንዳርጋቸው የተደረሰውን “ለአንቺ ነው ኢትዮጵያ” የሚለውን አገራዊ መዝሙር በአንድነት እየተዘመረ የተዘጋጀውን ኬክ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ሊቀመንበር በአቶ ዮሃንስ ዓለሙ ከወጣቶችና ሴቶች ተወካዮች ጋር በአንዳርጋቸው ስም በክብር እንዲቆርሱ ተደርጓል። ለቃል ኪዳን ይሆን ዘንድ ሁሉም የበዓሉ ታዳሚ ከኬኩ ተቋድሰዋል!



በአጠቃላይ የተከበረውና ያሰባሰበን ልዩ የልደት በዓል በዋናነት የኢትዮጵያን ህዝብ አንድ የአደረገ ብሎም የዓለምን ቀልብ የማረከ፣ አለም አቀፍ የዜና መገናኛዎችን ትኩረት የሳበ የአርበኛው አንዳርጋቸው ጽጌ ቢሆንም ለእነ እስክንድር ነጋ፣ ርእዮት ዓለሙ፣ አንዷለም አራጌ፣ አቡበከር፣ በቀለ ገርባ፣ ኦልባና ሌሊሳ፣ ውብሸት ታዬ፣ አበበ ቀስቶ፣ አበበ ካሴ፣ ኦኬሎ አኳይ፣ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን፣ አብረሃ ደስታ፣ ተመስገን ደሳለኝ እና ብዙ ጋዜጠኞች፣ እንዲሁም ብዙ ሽህ እስረኞች ለነጻነት ሲሉ በስቃይና በመከራ ለሚገኙ ሁሉ መታሰቢያ ጭምር ነበር።

  • ዛሬ ስለ አንዳርጋቸው የምንናገርበት፣ የምናወራበት፣ የምንመክርበት ብቻ አይደለም ይልቁንም በተግባር የምናሳይበት፣ ለዓላማው ቃል የምንገባበት፣ አጋርነታችንን የምናሳይበት እንጂ፤
  • ዛሬ ኬክ ለክብሩ ለልደቱ የተዘጋጀውን መቆረስ ብቻ አይደለም ማንነታችንን የምንፈትሽበት፣ ወኔያችንን የምንለካበት፣ ኢትዮጵያውነታችንን የምንመሰክርበት ወቅት፣ ጊዜና ስዓት ነው፤
  • ዛሬ አድነታችንን የምናጸናበት፣ ህብረታችንን የምንገልጽበት ልዩ ስዓት ነው
  • ዛሬ የራሳችንን ነጻነት በእራሳችን ለማስከበር ቆርጠን የምንነሳበት ቀን ነው፤ ስደት፣ እንግልት፣እስራት፣ሞት፣ተጨቋኝነት፣ የበታችነት ይብቃ የምንልበት ቀን ነው። 
  • ዛሬ ፍትህና ነጻነት ለተነፈጉ፣ ድምጻቸው ለታፈነ፣ መብታቸው ለተረገጠ፣ ማንነታቸውን ላጡ በአንድነት የምንቆምበት ወቅት ነው።
  • ዛሬ ሰባዊና ተፈጥሮአዊ መብታችንን ለማስከበር እራሳችንን አሳልፈን እስከ መስጠት ድረስ የምንታገልበት፣ የምንነሳበት፣ የምንወስንበት ቀን ነው። ምክንያቱም መብት ከለለ ሰውነት የለም፣ ነጻነት ከለለ ህይወት የለምና!እንስሳት እንኳ መብታቸውን የሚያስከብሩበት የራሳቸው ዜዴ አላቸው....እኛ ሰዎች ደግሞ ከእነርሱ የተለየን ውድ ፍጥረቶች ነንና!
ለምን ልደቱን እናከብራለን
  • ከልጅነት እስከ እውቀት ለእናት አገራችን ጊዜውን፣ እውቀቱንና የግል ህይወቱን መስዋዕት አድርጎ ያቀረበ ልዩ ፍጥረት ስለ ሆነ፣
  • አንድም ከአለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከብዙ ሺህ መንገደኞች መኳከል አለማቀፍ ህግን በጣሰ መልኩ መታፈኑ፣ 
  • አንድም ወያኔን ግራ ማጋባቱ፣ እንዳይፈቱት ፍርሃት እንዳያስሩት ጭንቀት ፈጥሮባቸዋል 
  • የቀደምት አርበኞችን ገድል ለአድሱ ትውልድ ለማስተላለፍ ድልድይ የሆነ ጎልማሳ አርበኛም ስለሆነ
  • በቤተሰብና በዘመድ፣ የታላቋ ብሪታንያ የፓርላማ ተወካዮች እንዳይጎበኙት መደረጉ እንዲሁም የህግ ጠበቃ አለመኖሩ 
  • ለዓላማው የፀና ብርቱና ኃያል ሰው ስለሆነ ነው እንዲሁም የይቅርታ አባት ኢትዮጵያዊ ማንዴላ ስለሆነ 
  • ደም ሳይፈስ መስዋዕት የለም እንዲሉ አንዳርጋቸውም እራሱን ለመስዋዕትነት አዘጋጅቶ የቀረበላቸው ለኢትዮጵያ ነጻነት፣ አንድነትና ክብር ሲል 
  • በጥቅሉ ተልኮውን ስለፈጸመ ነው! የአንዲ ተልእኮ ኢትዮጵያ ከወያኔ ሰው በላ ቡድን ነጻ የምትወጣበትን ቀን ማቅረብ ነበር፣ ከአለምንም ጥርጥር ጊዜው ቀርቧል 
  • አንዳርጌ የሚከበር ፣ የሚወደድና በአእምሮው ትልቅነት ፣ በሰብአዊነቱና በአርቆ አሳቢነቱ – ማናቸውንም የነጻነት መስዋዕ ትነት ለመክፈል ባሳየው ቆራጥነት የአንድየን ልደት ልዩ አድርጎን በድምቀት እንድናከብረው አድርጎናል። 
አንዳርጋቸው በአጭሩ፦
  • በተለይ ለወጣቱ ህይወቱን አሳልፎ ሰጦ በእስር ቤትም ሁኖ የነጻነትን ተስፋ የአስተላለፈ ታላቅ ጀግና ነው። 
  • የቀደሙ አባቶቻችን የአገርን ሉዓላዊነት፣ የሕዝቧን ደህንነት፣ዳርድንበሯንና ሙሉ ታሪኳን አስከብረውና ጠብቀው ለእኛ ለአሁኑ ትውልድ ለማስረከብ ውድ ሕይዎታቸውን በሰማእትነት ከፍለዋል፤ ደማቸውን አፍስሰዋል፤ አጥንታቸውን ከስክሰዋል። አንዳርጋቸውም የአባቶቹን ፈለግ ተከትሎ ውድ ህይወቱን ከፍሎ የአገርን ትልቅ አደራ ለእኛ አስተላልፏል። 
  • ስለዚህ አንዳርጋቸው የአበው የትግል ታሪክን ተቀብሎ ለአዲሱ ትውልድ አሻገረ!
  • የኢትዮጵያያን የሰላም፣የነጻነት ተስፋ ለትውልድ በራዕዩ አሳደረ!
  • ወያኔ ከሀዲዎችን አራቆተ ማንነታቸውን ገለጠ ህይወታቸውን አከሰረ!
  • ለነጻነት ለፍትህ ለዲሞክራሲ ለአንድነት ትግል ተጣራ እውነትን በዓለም አበሰረ!
  • ነፃነት ፍትህ ዲሞክራሲ ካልሰፈነ በቀላሉ የሚፈነዳ የዘላለም ቦምብን ቀበረ! ህዝባዊ እሳትን ጫረ!
  • አንዳርጋቸው የአንድነትን መስመር አሰመረ!
  • ድካሙ፣ ትግሉ ለአንቺ ነው ኢትዮጵያ ብሎ ኢትዮጵያውያንን በአገር ፍቅር፣ በአገር ስሜት አዘመረ!
  • በመወለዱ ህዝብ ሁሉ ደስ አለው እርሱም በልደቱ አማረ! 
  • እንደ ማንዴላ ኢትዮጵያውያንን በስራቱ ነጻ ለማውጣት ጉዞ ጀመረ!
  • አንዳርጋቸው አንድ አደረገን ኢትዮጵያ ነጻ ትውጣ ብሎ የአንድነትን ቃል ተናገረ!

ምን እናድርግ
·አንዳርጋቸውን እንሁን
· እርሱን እንላበስ፣ የእርሱን መንገድ እንከተል
· ፍርሃትን፣ አድር ባይነትን እናሶግድ
· አንዲ የሰጠንን ታላቅ አገራዊ ተልእኮ እንፈጽም
· ራዕዩን ከግብ ለማድረስ ቆርጠን እንነሳ፣ ቃል እንግባ!

ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆችዋ ተከብራ ትኖራለች!
አንዲ ራዕይህ እውን ይሆናል! ቀጣይ የልደት በዓልህ ላይ በአካል እንደምትገኝ በእምነት ተስፋ እናደርጋለን!!!

No comments:

Post a Comment