Thursday, October 2, 2014

አቶ ሰለሞን ገ/ስላሴ ከአሜሪካ ተባረሩ

የኢትዮጵያ ኢምባሲ ባልደረባ የሆኑት አቶ ሰለሞን ገ/ስላሴ በ 48  ከአሜሪካ እንዲወጡ ታዘዙ:: ከአሜሪካ እንደወጡም የዜና ምንጮች ገለጹ።

የኢትዮጵያ ኢምባሲ ባልደረባ የሆኑት አቶ ሰለሞን ገ/ስላሴ በ 48 ሰአት ውስጥ ከአሜሪካ እንዲወጡ ታዘዙ:: ከአሜሪካ ተባረሩ አሁን በደረሰን ዜና መሰረት
ሰኞ ረፋዱ ላይ ኢትዮጵያኖች በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞአቸውን በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ላይ ተገኝተው ድምጻቸውን በማሰማት ላይ እንዳሉ የኢምባሲው ባልደረባና የአቶ ግርማ ብሩ ዘበኛ የሆኑት በኢትዮጵያኖች ላይ ጥይት ከተኮሱ በኋላ በደህንነት አባላት ታስረው በዲፕሎማት መብት ቢለቀቁም በ48 ሰአት ውስጥ ከአሜሪካን ሀገር እንዲወጡ የአሜሪካን መንግስት ማዘዙን ምንጮች አስታውቀዋል። አቶ ሰለሞን ከአሜሪካ መባረረራቸውን ምንጮች በድጋሜ አረጋግጠዋል።

በእለቱ ምንም አይንት ጉዳት ባይደርስም የአሜሪካን የጸጥታ ሃይሎች ጉዳዩን እየመረመሩት መሆኑን ቃላአቃባዮ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ አረጋግጠዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከኢትዮጵያ ኢምባሲ ጋዜጠኛ ነው ተብሎ በስቴት ዲፓርትመንት የጋዜጠኞች መግለጫ ላይ የተላከው የህወሃቱ ዘጋቢ በእለቱ ጥያቄ አለኝ በማለት የአሜሪካን ፕሬዝዳንት በትክክል መናገር አለመቻሉ የአለም ጋዜጠኞችን እና የስቴት ዲፓርትመንትን ከማሳቁም ባለፈ በዲሞክራሲያዊት አሜሪካ የሚደረገውን ሰላማዊ ተቃውሞ በጋዜጠኞች ፊት መተቸቱ የህዋትን ኢሰባዊና ኢዲሞክራሲያዊ ድርጊትን ይበልጥ አጋልጧል። በቦታው የተገኙትን ጋዜጠኞችም የኢትዮጵያን መንግስት ጋዜጠኞች የመንግሥት ተላላኪዎች ብቻ እንጂ ብቃት የለሌላቸው መሆኑን ለመረዳት ተችሎል።

በዚህ ከተቀጠለ ኢትዮጵያ አገራችን የነጻነትን ብርሃን ለማየት እድል ሊያጋጥማት እንደሚችል ብዙዎች ይናገራሉ።

No comments:

Post a Comment