Sunday, October 26, 2014

ወጣቶች ስለአገራቸው ሰፊ ውይይት አካሄዱ (ኖርዌይ,ኦስሎ)

የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የወጣቶች ክፍል ቅዳሜ ጥቅምት 10/2007 ዓምኦክቶበር 25/2014ለአገር እድገትና ለድሞክራሲ ግንባታ የወጣቶች አስትዋጾ” በሚል ርዕስ ሰፊ ውይይት ከ15:00 እስከ 18:00 ስዓት ተካሄደ።
የመግቢያ ንግግሩ በድርጅቱ ህዝብ ግንኙነት በአቶ አቢ  አማረ የውይይቱን ዓላማና አስፈላጊነት ለተሳታፊው በመግለጽ ወጣቱ ትውልድ ለአገር እገድትና ዲሞክራሲያዊ ግንባታ ያለውን ከፍተኛ አስትዋጾ ሁሉም ተገንዝቦ የወያኔን አስከፊ ስርዓት ለመታገል በዚህ መልኩ  ውይይት መካሄዱ ሊበረታታ የሚችልና ውይይቱም ውጤት ሊያመጣ በሚችል መልኩ እንዲካሄድ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት ይኖርበታል ብለዋል።
በመቀጠልም በክፍሉ ተወካይ በወጣት ይበልጣል ጋሹ ለውይይቱ በሚጠቅም መልኩ የወጣቱን አስፈላጊነትና እንዴት ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ሰፊ ገለጻ ሰጧል። ከገለጸው ሃሳብም መካከል የአንድ አገር ቀጣይነት ያለው እድገት የሚለካው በአላት ሃብትና ንብረት ብቻ ሳይሆን ያንን ተረክቦ በአደራ ለትውልድ ማስተላለፍ የሚችል ትውልዳዊ ትስስር መኖርና ይህንንም እንደ ድልድይ ሆኖ  ከአንዱ ትውልድ ወደቀጣዩ ትውልድ የሚያስተላልፈው ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል እንደሆነ፤ በማንኛውም አገር፣ ጊዜና ዘመን እያንዳንዱ ተተኪ ትውልድ የአገሩ ወራሽ፣ ተተኪና ተረካቢ፣ ጠባቂና ለሚቀጥለውም ትውልድ የማውረስ፣ የማስተላልፍና የማስረከብ ኃላፊነትና ግደታ እንዳለበት፤ ወጣት ለአንድ አገር በሦስቱም ዘርፍ ማለትም በማህበራዊ፣  በምጣኔ ሃብታዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማድረግ እንደሚችል ተረድቶ ወጣቱ ትውልድ በዓላማ፣ በቁርጠኝነት፣ በዕቅድና በመደራጀት  ለአገር እድገት፣ ነጻነት፣ፍትህና ዲሞክራሲ መታገልና ለውጥ ማምጣት እንዳለበት ለውይይት እንደ መነሻ ባቀረበው ሃሳብ ላይ ገልጿል። እንዲሁም የወያኔን አስከፊ፣ ዘረኛና አምባገነናዊ ሥርዓት ለማስገወገድ  ወጣቱ ትውልድ የበኩሉን ሃላፊነት ወስዶ ይህን  ለአገርና ለህዝብ መቆም እንዳለበት በመግለጽ የውይይት ሃሳቦችን አስቀምጦ ስዓቱን ለውይይት ክፍት አድርጓል። ወጣቱንም በሦስት ክፍል ለመክፈል ሞክሯል። እነሱም 1. ወጣትነትን ተጠቅሞ ለአገሩ የሚያስብ የሚጨነቅ፣ አገራዊ ስሜት ያለው፣ የለውጥ ኃይል የሆነ፣ ለነጻነትም የሚታገል፣ለአገር እድገትና ዲሞክራሲ ግንባታ የሚፋጠኑ፤ 2. አገሩን የማያውቅ፣ ማንነቱን የረሳ፣ ማዎቅም የማይፈልግ፣ ለጠቅም ብቻ የሚጓዝ እና 3. በስሜት የሚጋዝ፣ ከነፈሰውና ከሞቀው ጋር የሚጓዝ ዓላማና ግብ የሌለው በማለት ከተናገሩ በኋላ ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ይህን ተገንዝቦ እራሱን ከጥቅምና አድር ባይነት አርቆ ለአገር በሚጠቅም መልኩ እራሱን ማነጽና ማስኬድ እንዳለበት አሳስቧል።
በውይይቱም በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ወጣቱ ለክፉም ለመልካምም የራሱ የሆነ ትልቅ አገራዊ ታሪክ እንዳለው በመግለፅ  ወጣቱ እንዴት መታገልና ለውጥ ማምጣት እንደሚችል ገንቢ አስትያየቶች፣ ምክሮችና አቅጣጫ ተሰጠዋል። ከተነሱትት ሃሳቦች መካከልም በበቂ ሁኔታ መደራጀት፣ በእውቀት እራስን ማብቃት፣ አገራዊ ስሜት መላበስ፣ታሪክን ጠንቅቆ ማዎቅ፣ አንድነት መፍጠር፣ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ስልታዊ እቅድ መከተል፣ አቀራረባችንን እና ትኩረታችን መለየት፣ ቀጣይነት ያላቸው የውይይት መድረኮችን ማዘጋጀት እና ክፍሉን ማደራጀት ከተነሱት አበይት ሃሳቦች መካከል ነበሩ። በተጨማሪም ክፍሉ ከሌሎች የወጣት ህብረት ጋር ግንኙነት በመፍጠር ልምድና ተሞክሮ  በመለዋወጥ ወጣቱን ይበልጥ ማንቃትና ፖለቲካዊ አድማሱን ማስፋትና የወያኔን ጨቋን መንግሥት ሊታገል የሚችልበትን አቅጣጫ ማሳየትና መንደፍ ተገቢ መሆኑን አጽንኦት ተሰጦበታል። 
በአጠቃላይ  ወጣቶች ለአገር እድገት፣ ለነጻነት፣ ለሰባዊ መብት፣ ለፍትህና ለዲሞክራሲ ግንባታ የወጣቱ አስትዋጾ ከፍተኛ መሆኑን ተረድቶ በሁለገብ ትግል ወያኔን/ ሕወሓትን ለማስወገድ የበኩሉን ኃላፊነትና ግዴታ መወጣት እንዳለበት በሥፋት ተገልጿል። ክፍሉም የተሰጠውን አስተያየት እና ምክር ተግባራዊ ለማድረግ የድርሻውን እንደሚወጣና ወያኔን ለመታገል በማነኛም መልኩ ዝግጁ እንደሆነ አሳውቋል።
በመጨረሻም  አቶ ልዑል ታደሰ ውይይቱ መልካምና ሂደቱም ጥሩና የተሳካ መሆኑን ገልጸው ለተሰብሳው ክፍሉን በሁሉም አቅጣጫ መደገፍና ማጠናከር ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የሚጠበቅ መሆኑን አስረድተዋል።  እንዲህ አይነት ውይይት በተለይ ለወጣቱ አስፈላጊና አስተማሪ ስለሆነ ቀጣይነት እንዲኖረው በተሳታፊዎች አስትያየት ተሰጦ ውይይቱ  ተጠናቋል።


ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ወጣቶች ክፍል

No comments:

Post a Comment